ግዙፉ ዓለም አቀፍ የችርቻሮ ኩባንያ በኢትዮጵያ ገበያ ለመሰማራት አቅዷል

Date:

በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞችን የሚያስተናግድ ዓለም አቀፍ ተቋም ነው

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ግዙፉ የችርቻሮና የጅምላ ንግድ ኩባንያ ከሆነው ካርፉር (Carrefour) ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ። ውይይቱ ካርፉር በኢትዮጵያ በጅምላና ችርቻሮ ንግድ ላይ ሊሰማራ በሚችልበት ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን  ኮሚሽነር ዶክተር ዘለቀ ተመስገን፣ ለካርፉር ተወካዮች ኢትዮጵያ በቅርቡ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ስላደረገቻቸው አዳዲስ የኢንቨስትመንት ዘርፎችና አማራጮች  ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።

የካርፉር (Carrefour) አለም አቀፍ ፍራንቻይዝ ዳይሬክተር  ኤማ ኮፔይ፤ የኢትዮጵያን ገበያ ለረጅም ጊዜ እንደ መዳረሻ ሲመለከቷት እንደነበር ገልጸው፣ የወጪና ገቢ ንግድ ዘርፉ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት መደረጉ ምቹ አጋጣሚ መፍጠሩን ተናግረዋል።

የኩባንያው ኮሜርሻል ዳይሬክተር ጄሮም ቦንዚ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመሰማራት የሚያስችል የቢዝነስ ሞዴል እያዘጋጁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። አክለውም፣  ዕቅዱን ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚያስችል ቡድን በቅርቡ ወደ አገር ውስጥ እንደሚልኩ ማስታወቃቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል።

እ.ኤ.አ  በ1959 ዓ.ም. በፈረንሳይ የተመሰረተው ካርፉር በአውሮፓ፣ እስያ፣ አፍሪካና ላቲን አሜሪካ በሚገኙ ሱፐር ማርኬቶቹ በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞችን የሚያስተናግድ ዓለም አቀፍ ተቋም ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...