የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ 12 ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ተከብሮ ዋለ!

Date:

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 12ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በዛሬው ዕለት ተከብሮ ውሏል።

በበዓሉ ላይ ያሬዳዊ ዝማሬዎች ፣ ቅኔ እና ሌሎች መርሐግብሮች የቀረቡ ሲሆን ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህርዳርና ሰሜን ጎጃም ሊቀ ጳጳስ ለቅዱስነታቸው የእንኳን አደረስዎ መልእክት አስተላልፈዋል።

በበዓሉ ላይ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የመምሪያ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች እና የውጭ ሀገር አምባሳደሮችና ተወካዮች እና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ተገኝተዋል።

በመጨረሻም ቅዱስነታቸው አባታዊ መልዕክትና ቃለ ምዕዳን አስተላልፈው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡

ቅዱስነታቸው የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በተካሄደው በዓለ ሲመት በቃለ መሐላ ሐዋርያዊ ኃላፊነት የተረከቡ ሲሆን ፤ በርካታ መንፈሳዊ እና ሀገራዊ ተግባራትን እንዲሁም ሐዋርያዊ ጉዞዎችን እያከናወኑ ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...