የመንግሥት ሠራተኞች የጤና መድን ተጠቃሚ ሊሆኑ ነው

Date:

የመንግሥት ሠራተኞች በቀጣዩ 2019 ዓ.ም የጤና መድን አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ጤና መድን አገልግሎት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ጤና መድን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ወርቁ እንደገለጹት፤ መደበኛ በሆኑ የሥራ መስኮች የተሰማሩ ዜጎች የጤና መድን አገልግሎት እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀው የማኅበራዊ ጤና መድን አገልግሎት በአዋጅና ደንብ ከጸደቀ 14 ዓመታትን አስቆጥሯል።

አዋጁ ሠራተኛው ከደመወዙ  ሦስት  በመቶው እንዲቆረጥና  የፌዴራልና የክልል መንግሥታትም ለቀጠሩት ሠራተኛ ሦስት በመቶውን እንዲሸፍኑ ይደነግጋል።

ሆኖም ግን ባለፉት ዓመታት በመንግሥት በኩል በቂ ገንዘብ ባለመኖሩና በኑሮ ዉድነት አማካኝነት ሳይተገበር ቢቆይም በዘንድሮዉ ዓመት ግን የተሻለ ተስፋ ታይቷል ብለዋል።

በዘንድሮው ዓመት በጤናው ዘርፍ የተሰማሩ ከ500 ሺህ በላይ ሠራተኞች ለአገልግሎቱ መመዝገባቸውን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፤  ከገንዘብ ሚኒስቴርም 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መጽደቁን ተናግረዋል።

በሚቀጥለው ዓመትም ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ ተጠቃሚ እንዲሆን የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግሥታት በጀት ይይዛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...