አዋሽ ባንክ ታሪካዊ የሆነውን 1000ኛ ቅርንጫፉን አስመረቀ

Date:

በግል ባንክ ኢንዱስትሪ ፈር ቀዳጅ በመሆን በአምስት ቅርንጫፎች ስራ የጀመረው አዋሽ ባንክ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጃርሶ ወረዳ ኤጀርሰ ጎሮ ከተማ 1000ኛ ቅርንጫፉን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሃይ ሽፈራውን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት አካላት እና እንግዶች በተገኙበት በይፋ አስመርቋል።

አዋሽ ባንክ በመላ አገሪቱ ቅርንጫፎቹን በማስፋፋት ህብረተሰቡ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችንበአቅራቢያው እንዲያገኝ በማስቻል በአሁን ወቅት የደንበኞቹን ብዛት ከ16.3 ሚሊዮን በላይ አድርሷል፡፡

በተጨማሪም ለአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት እና ለሕብረተሰቡ የኑሮ መሻሻል የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት በፋይናንስ ኢንዱስትሪው የበኩሉን አስተዋፅኦ በመወጣት ላይ እንደሚገኝ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሃይ ሽፈራው በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ገልፀዋል፡፡

ባንኩ ከመደኛው የባንክ አገልግሎት ሰጪ ቅርንጫፎች በተጨማሪ ደንበኞችን ማዕከል ባደረጉ ከወለደ ነጻ የባንክ አገልግሎትና በዲጂታል ቅርንጫፎች (e-Branch) በመታገዝ ዘመኑን የዋጁ ቀልጣፋ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል።

አዋሽ ባንክ የጃርሶ ቅርንጫፍን ከመክፈት በተጨማሪ የአካባቢውን ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለሀገር ብዙ ውለታ የዋሉ የሀገር ባለውለታዎች ላፈራው ለጃርሶ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ግምታቸው በብር አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ዋጋ የሚያወጡ ብዛታቸው 25 የሆኑ ኮምፒዩተሮችን አበርክቷል።

ከዚህም በተጨማሪ የኤጀርሳ ጎሮ ከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ አና የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የከርሰ ምድር የውሃ ቁፋሮ ፕሮጀክት ለማከናወን ባንኩ በጀት የመደበ ሲሆን የፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ የመሰረተ ድንጋይም በዛሬው እለት ተቀምጧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...