በአዲስ አበባ ከተማ ጥር 10 እና 11 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚከበረዉ የከተራና የጥምቀት በዓል ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ይፋ አድርጓል፡፡
በጃን ሜዳ፣ በአቃቂ ቃሊቲ ጥሩነሽ ቤይጂንግ፣ በለሚ ኩራ አራብሳ ሠፈራ እንዲሁም በን/ስ/ላፍቶ ሀጫሉ አደባባይ አካባቢ በሚገኙ ጥምቀተ ባህር ቦታዎች በርካታ ታቦታት ስለሚያድሩና የበዓሉ አክባሪዎች ስለሚወጡ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፦
ከፈረንሳይ ለጋሲዮን ወደ 6 ኪሎ (ፈረንሳይ ኤምባሲ ድልድይ )
ከቀበና አደባባይ ወደ ምኒልክ ሆስፒታል (ቀበና አደባባይ )
ከጀርመን ኤምባሲ ድልድይ ወደ ምኒልክ ሆስፒታል (ጀርመን ኤምባሲ ድልድይ )
ከኮሪያ ሰፈር ወደ ምኒልክ (ኮሪያ ሰፈር)
ከግንፍሌ ወደ ሳንፎርድ ት/ቤት (ግንፍሌ ድልድይ)
ከቅድስት ማርያም ወደ ጃንሜዳ (ቅድስተ ማርያም )
ከገንዘብ ሚ/ር ወደ 6ኪሎ ቶታል (ገንዘብ ሚ/ር)
ከ6 ኪሎ አደባባይ ወደ ፈረንሳይ ለጋሲዮን (6ኪሎ አደባባይ ላይ )
ከቃሊቲ ማሰልጠኛ ጥሩነሽ ቤጂንግ
ከዩኒሳ በዓለም ባንክ ጥሩነሽ ቤጂንግ
ከኮዬ አደባባይ በዋሊያ ጥሩነሽ ቤጂንግ
ለሚ ኩራ አራብሳ ሠፈራ አካባቢ
ን/ስ/ላፍቶ ሀጫሉ አደባባይ አካባቢ
ከጥር 10 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 5:30 ጀምሮ በዓሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ መንገዶች የሚዘጉ ሲሆን አሽከርካሪዎች ታቦታቱ በሚያልፉባቸው ቦታዎች መንገዶች ዝግ መሆናቸውን አውቀው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
