ኢራን የኒኩሌር ስምምነት ካላደረገች መከራ  ይዘንብባታል

Date:



የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ኒኩሌር ስምምነት ድርርድር እንድትመለስ አስጠነቀቁ ፥ ያ ካልሆነ ብርቱ ወታደራዊ ጥቃት ሊከተል እንደሚችል ዝተዋል ።

ፕሬዚደንቱ ሶሻል ትሩዝ በተሰኘው የግል የማኅበራዊ መገናኛ መድረካቸው ዛሬ ይፋ እንዳደረጉት ከሆነ «ጊዜው እያከተመ ነው» ብለዋል ።

ኢራን ቀደም ሲል ከእኔ ጋር ስምምነት ባለመፈጸሟ «ተልእኮ የእኩለ ሌሊት መዶሻ» የተሰኘው እጅግ ብርቱ ጥቃት ነው የደረሰባት ያሉት ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ያሁኑ የከፋ ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል ። 

ባለፈው ኢራን ከሥራኤል ጋር ለ12 ቀናት ባደረገችው ጦርነት በ«ተልእኮ የእኩለ ሌሊት መዶሻ» የኢራን የአቶም ተቋምን የዩናይትድ ስቴትስ ጄቶች ከራዳር ዕይታ ውጪ በመብረር በቦንብ ደጋግመው ደብድበው ነበር ።

«አማንዳ» የተሰኘችው የዩናይትድ ስቴትስ በርካታ የጦር ጄቶች ተሸካሚ ግዙፍ የጦር መርከብም ወደ ኢራን አቅጣጫ እየቀዘፈች መሆኑን ዶናልድ ትራምፕ ተናግረው ነበር ።

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር መሥሪያ ቤት በበኩሉ የዩናይትድ ስቴትስ ሥጋት ከቀጠለ በዋሽንግተን እና ቴህራን መካከል ድርድር ሊኖር እንደማይችል አሳውቋል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...