የወሰን ማስከበር እየፈተነው እንደሆነ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ባሉ የመንገድ ግንባታ ሂደቶች ውስጥ፣ የወሰን ማስከበር ጉዳይ ዋነኛው ተግዳሮት እንደሆነበት የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኢያሱ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

አዲስ አበባ ቀድማ የለማች ከተማ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ በመንገድ ግንባታ ወቅት ከፍተኛ የወሰን ማስከበር ችግሮች ያጋጥማሉ ያሉ ሲሆን በተለይም ነባር መንገዶችን የማስፋፋትና አዳዲስ መንገዶችን የመገንባት ሥራዎች በከተማዋ የእድገት ደረጃ ልክ ለማከናወን እንቅፋቶች እየፈጠሩ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

እንደ ዳይሬክተሩ ማብራሪያ፣ በግንባታው ዘርፍ የሚታዩት ችግሮች ከከተማዋ ነባራዊ ሁኔታና ከመሠረተ ልማት ዝርጋታ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ጠቁመው ነባር መንገዶች ቀደም ሲል የነበረውን አነስተኛ የትራፊክ ፍሰት ታሳቢ በማድረግ የተገነቡ በመሆናቸው፣ አሁን ካለው የከተማዋ እድገት ጋር ለማጣጣም የግድ ማስፋፊያ ያስፈልጋቸዋል በዚህም ምክንያት የሚነሱ ለሚደረጉ ማስፋፊያዎች የወሰን ማስከበር ስራ ለተቋሙ ፈታኝ እንደሆነበት ገልጸዋል።

በመንገድ ወሰን ላይ የሚገኙ የውኃ፣ የኤሌክትሪክና የሌሎች ተቋማት መሠረተ ልማቶችን፣ ቤቶችንና ልዩ ልዩ ግንባታዎችን የማንሳት ሥራ ከፍተኛ ውጣ ውረድ ያለበት መሆኑ ጠቅሰው በወሰን ማስከበር ሂደት ውስጥ የሚታዩት እነዚህ ውስብስብ ሁኔታዎች በመደበኛው የመንገድ ግንባታ ፍጥነት ላይ ጫና ማሳደራቸውን ጠቁመዋል።

ባለሥልጣኑ እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው በመፍትሔነት እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች ከአስተዳደር አካላትና ከመሠረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ለችግሮቹ ፈጣን መፍትሔ የመስጠት ሥራ መጠናከሩን ገልጸዋል።

በኮሪደር ልማቱ የተገኘውን መልካም የቅንጅት ተሞክሮ ወደ መደበኛው የመንገድ ግንባታ ሥራ በማምጣት፣ ግንባታዎች ሳይስተጓጎሉ እንዲጠናቀቁ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

አሐዱ ራዲዮ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...