የእቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ የወርቅ የፀጉር ጌጥ ወደ እናት ሀገሩ ተመለሰ

Date:

ከ150 ዓመታት በፊት በመቅደላ ጦርነት ወቅት በእንግሊዝ ወታደሮች ተዘርፎ ከሀገር የወጣውና የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ባለቤት የእቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ ንብረት የሆነው ታሪካዊ የወርቅ የፀጉር ጌጥ በይፋ ለኢትዮጵያ ተመልሷል።

መጋቢት 7 ቀን 2026 እ.ኤ.አ. በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የአሜሪካ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ሙለን ላይብረሪ በተካሄደ ደማቅ ሥነ-ሥርዓት፣ “ትውስታ፣ ማጣት እና የንጉሣዊ ቅርስ መመለስ” በሚል መሪ ቃል ቅርሱ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ቀርቧል።

የሮያል ኢትዮጵያ ትረስት መሥራች ልዑል ኤርምያስ ሳህለ ሥላሴ ቅርሱን በይፋ የገለጡ ሲሆን፣ ክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለምና የታሪክ ተመራማሪው ዶክተር አሉላ ፓንክረስት ስለ እቴጌዋ ሕይወትና ስለ ቅርሱ ታሪካዊ ፋይዳ ጥልቅ ትንተና ሰጥተዋል።

በ1860ዎቹ አጋማሽ ከመቅደላ ከተዘረፉ በርካታ ቅርሶች አንዱ የሆነው ይህ ጌጥ መመለሱ፣ ወደ ውጭ የተወሰዱ የኢትዮጵያ ቅርሶችን ለማስመለስ ለሚደረገው ብሔራዊ ጥረት ትልቅ ስኬትና መነቃቃት ተደርጎ ተወስዷል።

የሮያል ኢትዮጵያ ትረስት ቅርሱን በማስመለስ ረገድ ላደረገው ከፍተኛ ተጋድሎም በዕለቱ አድናቆት ተችሮታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...