ታዋቂው ደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ 10ኛ ልብወለድ እና 18ኛ መጽሐፍ የሆነው ፈሪሳ የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ቅዳሜ መጋቢት 5 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በደመቀ ሁኔታ ለምረቃ በቅቷል።
በደመቀው የምረቃ መርሃ ግብር ላይ ግሩም ዘነበ መድረኩን የመራው ሲሆን፣ አንጋፋው አርቲስት አበበ ባልቻ እና የማስታወቂያ ባለሙያው ሳምሶም ማሞ ከመጽሐፉ ላይ የተመረጡ ገጾችን ለታዳሚው አንብበዋል።
በተጨማሪም ታዋቂው ሐያሲ ቴዎድሮስ አጥላው ስለመጽሐፉ አጠቃላይ ይዘትና ኪነ ጥበባዊ ጥንካሬ አስተያየቱን አቅርቧል።
ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም፣ ገጣሚት ምልዕቲ ኪሮስ እና ገጣሚ ደምሰው ግጥሞቻቸውን ለታዳሚው አቅርበዋል።
ፈሪሳ የደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ 18ኛ መጽሐፍ ሲሆን በልብወለድ ደረጃ ደግሞ 10ኛው ነው። ደራሲው ለንባብ ያበቃው ይህ አዲስ ሥራ ከዛሬ ጀምሮ በሁሉም የመጽሐፍ መደብሮች ለገበያ ቀርቧል።
