ኤም-ፔሳ ኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት የመጀመሪያውን ስምምነት ተፈራረመ

Date:

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የታክስ ክፍያዎችን በኤም-ፔሳ የዲጂታል ስርዓት ለመሰብሰብ የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ ተፈራርሟል።

ስምምነቱ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢ በሆነው ኤምፔሳ ኢትዮጵያ እና የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ መሀከል በባህር ዳር ከተማ ተፈርሟል።

ግብር ከፋዮች ከዚህ በውሃላ ኤም-ፔሳን በመጠቀም ግብራቸውን ካሉበት ሆነው በዲጂታል አማራጭ በቀላሉ መክፈል ይችላሉ ተብሏል።

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2017 የግብር ዘመን 67 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ መንገሻ ፈንታው(ዶ.ር) ተናግረዋል።

በ2018 በጀት ዓመትም ክልሉ 100.37 ቢሊየን ብር የመሰብሰብ እቅድ አለው፣ ከዚህ ውስጥ እስካሁን 60 በመቶ የሚሆነውን ሰብስቧል ብለዋል።

በክልሉ ያሉ ግብር ከፋዮች ከ477 ሺህ በላይ መሆናቸውም ተነግሯል።

የታቀደውን ገቢ መሰብሰብ የሚቻለው በዲጂታል አማራጭ በመታገዝ ግብርን በቀላሉና በቀለጠፈ መንገድ መሰብሰብ ሲቻል ነው ብለዋል የቢሮኤ ሃላፊ።

ከኤም-ፔሳ ኢትዮጵያ ጋር ዛሬ የተፈረመው ስምምነትም ይህንን የማሳካቱን ጉዞ የሚያግዝ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህ የጋራ ስምምነት በአማራ ክልል የሚገኙ ግብር ከፋዮች ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ፈጣን እና ምቹ የታክስ ክፍያዎችን ባሉበት ሆነው በኤም-ፔሳ በኩል መፈጸም ይችላሉ ብለዋል።

የኤም-ፔሳ ኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ጌታቸው መንግስቴ፣ ኤም ፔሳ የፋይናንስ ስርዓትን ለማገዝ የሚያስችለውን ስምምነት ከመንግስት ባለ በጀት ተቋማት ጋር ሲፈፅም የአሁኑ የመጀመሪያው መሆኑን ተናግረዋል።

እዚህ ስምምነት ላይ ለመድረስ ብዙ ሂደትን ማለፍ ነበረብን ብለዋል አቶ ጌታቸው።

የገንዘብ ሚኒስቴር ያፀደቀው አዲስ መመሪያ፣ በብሔራዊ ባንክ እውቅና ያላቸው የፋናንስ አቀላጣፊ ተቋማት ከመንግስት ባለ በጀት ተቋማት ጋርም መስራት እንዲችሉ ይፈቅዳል፤ የመንግስት ተቋማት ለዚህ ዝግጁ መሆን አለባቸው ይላል ብለዋል።

ይህም እንደ ኤም-ፔሳ ያሉት ተቋማት ስራቸውን ወደ መንግስት ተቋማትም እንዲያሰፉ እድል የሚሰጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ኤም-ፔሳ ኢትዮጵያ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አካል ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ የራሱ ህጋዊ ሰውነት ኖሮት ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በመውሰድ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል።

በአሁኑ ሰዓትም በዚሁ የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓት ከውሃና መብራት ክፍያ ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቲኬት ክፍያ፣ገንዘብ ወጪና ገቢ ማድረግ ያሉ አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑ ተወርቷል።

ተቋሙ በሶስት ወራት ውስጥ ሲም ካርዳቸውን የተጠቀሙ ደንበኞቹን የ90 ቀናት ንቁ ደንበኞች ብሎ የሚመዘግብ ሲሆን የዲጂታል ፋይናንስ ንቁ ደንበኞቹ ቁጥርም አምስት ሚሊየን መሻገሩን ተናግሯል።

የሳፋሪኮም የቴሌኮም ደንበኞቹ ቁጥርም ከ12 ሚሊየን በላይ ደርሷል ተብሏል።

በመላው ኢትዮጵያ የአገልግሎት ተደራሽነቴን አስፍቻለው ያለው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በመላው ሀገሪቱ 3500 የኔትዎርክ ማማዎችን እስካሁን ዘርግቻለውም ብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምርጫ ለሰላም ግንባታ

ግዮን መጽሔት :-ለኢትዮጵያ ሰላም ምርጫ አማራጭ የሌለው መንገድ ነው።...

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከባለፈው  ዓመት የ130 በመቶ ብልጫ  አተረፈ

መጋቢት 30 በተጠናቀቀው የኩባንያው በጀት ዓመት 15.9 ቢሊዮን ብር...

በዕውቀቱ በታላቁ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ተመረጠ

ዝነኛው ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...