ኢትዮ ቴሌኮም እና ማስተር ካርድ የዲጂታል ውይይት አደረጉ  

Date:

በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እና የማስተርካርድ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ማርክ ኤሊዮት የተመራ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች ልዑክ በኢትዮጵያ አዳዲስ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማስጀመር የትብብር እድሎችን ለመፈተሽ የሚያስችል ውይይት አካሄዱ።

ይህ የትብብር ማእቀፍ የቴሌብርን እና የማስተርካርድን ፕላትፎርሞችን በመጠቀም የዲጂታል ፋይናንስ ሶሉሽኖችን ለማሳደግ፣ የፋይናንስ ተደራሽነትን በከፍተኛ ሁኔታ ለማስፋት እና ዘላቂ እድገትን ለማበረታታት ያለመ ነው።

ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ኢትዮ ቴሌኮም በአፍሪካ ትልቅ የደንበኞች ቁጥር እና ግዙፍ መሠረተ ልማት ያለው በመሆኑ ይህም አዳዲስ እድሎችን ለመክፈት የሚያስችል አስቻይ ሁኔታ እንደፈጠረለት በማብራራት በአጋርነት ለመስራት ያላቸውን ተነሳሽነት አረጋግጠዋል።

የማስተርካርድ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ማርክ ኤሊዮት በበኩላቸው የኢትዮ ቴሌኮም ፈጣን የደንበኞች ቁጥር ዕድገት እና ግዙፍ የመሰረተ ልማት አቅም ለአጋርነት ተመራጭ እንደሚያደርገው በማረጋገጥ ማስተርካርድ ይህ ትብብር መልካም አጋጣሚ የፈጠረለት መሆኑን እና ለተግባራዊነቱ ያላቸውን የላቀ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ይህ ስትራቴጂያዊ ትብብር ሀገራችንን በዓለም አቀፍ ዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ያላትን ተወዳዳሪነት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግ ሲሆን ዘላቂ ዕድገትንና የሀብት ፈጠራን በማበረታታት አካታች እና ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ፋይናንስ ምህዳር እንዲሁም ዘላቂ እድገት ለማስመዝገብ ያስችላል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...