ጥራት እና ደህንነታቸው ያልተረጋገጡ ስለሆኑ እንዳትጠቀሙ ” – ባለስልጣን መ

Date:

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአዲስ አበባ ሁሉም ክ/ከተሞች እና በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ከተሞች ማለትም ፦
– አዳማ
– ቢሾፍቱ
– ዱከም
– ሰበታ
– ቡራዩ
– ሱሉልታ
– ለገጣፎ
– ገላን በሚገኙ 570 የንግድ ተቋማት ላይ ባደረገው ፍተሻ አስገዳጅ የጥራትና የገላጭ ጽሁፍ መስፈርቶችን (CES 73) ያላሟሉ ሕገ-ወጥ ምርቶች በገበያ ላይ መገኘታቸውን ገልጿል።

ህብረተሰቡ ጥራትና ደህንነታቸው ያልተረጋገጡ የሚከተሉትን ምርቶች እንዳይጠቀም ባለስልጣኑ አሳስቧል።

1. የገበታ ጨው (32 ዓይነቶች) ፦ ሰይፋ፣ ቲና፣ እሙሹ፣ ቃሊ፣ አዮዲን፣ እኑ፣ አራዳ፣ ንጉስ፣ ሀሮት፣ ኩል፣ አሜን፣ ሰቦኑማ፣ እቱ፣ መክሊት፣ ዳግም፣ መርሰን፣ ኒሀል፣ ሊቅ፣ ስካይ፣ ናፊ፣ አቤ፣ ሳሮማ፣ ፀሐይ፣ ማሩ፣ ንጉስ፣ እንቁ፣ ሰኒ፣ ሚያዋ፣ ስኬት፣ ሔራል፣ ቤዝ እና ገዳ

2.የምግብ ዘይት (19 ዓይነቶች) ፦ ምስራቅ ፀሐይ፣ ቃል፣ አፍራን፣ ኒያ፣ ሪሃ፣ ኤአይ ሻኪር፣ ኤ1-ኑር፣ ጥራ፣ ረዲ፣ አያን፣ ሳፊያ፣ እሰይ የተጣራ ፣ አማን፣ ላምሮት ኬኬ፣ እድገት፣ ራኒያ፣ ሸገር፣ ሀይላለ እና ፍፁም የተጣራ

3.የለውዝ ቅቤ ፦ ሀራ ፣ ሶራ፣ ብሉ፣ ስዊት ክሬም፣ ሉሲ እና ስንቅ

4. ማር ፦ ቤዛ፣ ውብሸት የማር ጠጅ ፣ ጂጂ፣ አምባሰል እና የኢሉባቦር ማር

5. ከረሜላ ፦: ቡርቃ ሎሊፖፕ፣ አዩ ፓፕ፣ አፍሪ እና ዴሉክሴ ከረሜላዎች፤

ባለስልጣን መ/ቤቱ እነዚህ መስፈርቱን የማያሟሉ፣ በመስሪያ ቤቱ ያልተመዘገቡ፣ ጥራትና ደህንነታቸው ያልተረጋገጡ ሕገ-ወጥ የምግብ ምርቶች ናቸው ፤ ” ህብረተሰባችን እንዳይጠቀማቸው ” ብሏል።

ምርት ሲገዙ ሊሟሉ የሚገቡ መስፈርቶችምንድናቸው ?

– በግልጽ የሚታይ ገላጭ ጽሁፍ ሊኖራቸው ይገባል።
– የአምራች ድርጅት ስም እና ሙሉ አድራሻ።
– የምርቱ የወል ስም ፣ የምርቱ ክብደት፣ የተመረተበትና የሚያበቃበት ቀን።
– መለያ ቁጥር (Batch Number) ችግር ቢገኝ ምርቱ ተለይቶ የሚታወቅበት መለያ።
– አስገዳጅ የጥራት ደረጃ ምልክት።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...