Uncategorized የኢትዮጵያ ብር እና የደቡብ ሱዳን ፓውንድ በዓለም ላይ ደካማ አፈጻጸም ካሳዩት ተርታ ተመደቡ በ ግዮን መጽሔት Date: 2026-04-11 የኢትዮጵያ ብር እና የደቡብ ሱዳን ፓውንድ እ.ኤ.አ በ2025 (ከታኅሣሥ 2017 እስከ ታኅሣሥ 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ) እያንዳንዳቸው ከ10 በመቶ በላይ ዋጋቸውን በማጣት በዓለም ላይ ደካማ አፈጻጸም ካሳዩ የመገበያያ ገንዘቦች ተርታ ተመደቡ። ኢትዮጵያ ውስብስብ በሆነ የዕዳ ሽግሽግ ሂደት ውስጥ ኢኮኖሚዋን ለማረጋጋት በምትታገልበት በዚህ ወቅት፤ ብር ከአርጀንቲና ፔሶ እና ከቱርክ ሊራ በመቀጠል በዓለም ሦስተኛው ደካማ የመገበያያ ገንዘብ ሆኖ ተመዝግቧል። የኢትዮጵያ መገበያያ ብር ከአሜሪካ ዶላር አንጻር 18 በመቶ ዋጋውን ያጣው በዶላር እጥረት፣ በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና በበውጭ ኢንቨስተሮች እምነት መቀነስ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።የዓለም ባንክን የመጋቢት 2018 ዓ.ም (April 2026) ወቅታዊ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ሪፖርት ዋቢ በማድረግ “ዘ ኢስት አፍሪካን” ጋዜጣ እንደዘገበው፤ ከዶላር አንጻር ሲሰላ፣ የኢትዮጵያ ብር 18 በመቶ እንዲሁም የደቡብ ሱዳን ፓውንድ 15 በመቶ ዓመታዊ የምንዛሬ አቅማቸውን አጥተዋል። ባንኩ ለደቡብ ሱዳን ፓውንድ መዳከም በጁባ የነዳጅ ወጪ ንግድ መስተጓጎልን እና በትይዩ (ጥቁር) ገበያ መካከል ያለውን የዋጋ ልዩነት እንደ ምክንያት ጠቅሷል። ኢኮኖሚስቶች እንደሚሉት፣ የገንዘብ ምንዛሬ ገበያ አለመረጋጋት በመላው አፍሪካ ለኢንቨስትመንት ትልቅ እንቅፋት ሆኖ ቀጥሏል። የመገበያያ ገንዘብ አለመረጋጋት ደግሞ ተጨማሪ መዘዝ እንዳለው ብዙዎች ደጋግመው ያስጠነቅቃሉ። ድንገተኛ የምንዛሬ ዋጋ መለዋወጥ፣ የውጭ ኢንቨስተሮች ‘ትርፋችን በኪሳራ ይዋጣል’ ብለው እንዲሰጉ ያስገድዳል። በተመሳሳይ የገቢ ዕቃዎች ዋጋ እና የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች በከፍተኛ ሁኔታ በሚዋዥቁበት ወቅት የአገር ውስጥ ነጋዴዎች ዕቅድ ለማውጣት ወይም ሥራቸውን ለማስፋፋት ይቸገራሉ።ለውጭ ኢንቨስተሮች በወራት ውስጥ የሚከሰት ከፍተኛ የምንዛሬ ኪሳራ ያገኙትን ትርፍ ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋው ይችላል። ለአገር ውስጥ ነጋዴዎች ደግሞ በተለይ የገቢ ዕቃዎች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በሚቀያየርበት ሁኔታ የወደፊት ዕቅድ ማውጣት የማይቻል ያደርገዋል።እነዚህ ጫናዎች ደካማ የመገበያያ ገንዘብ ያላቸው ሀገራት ለምን የረጅም ጊዜ ካፒታልን ለመሳብ እንደሚቸገሩ ማብራሪያ ይሆናሉ ተብሏል። አስ ቀዳሚ ጽሑፍየኢራን ጠቅላይ መሪ የደረሰባቸው ከፍተኛ እና አካል የሚያጎድል ጉዳት እንደሆነ ተዘገበቀጣይ ጥሑፍአሜሪካ የኢራን ወደቦቸን ከሰኞ ጀምሮ እንደምትዘጋ አስታወቀች ያጋሩ! FacebookTwitterWhatsAppTelegram መጽሔቶች ግዮን መጽሔት ቅጽ 8 ቁጥር 231 2026-06-12 ግዮን መጽሔት ቅጽ 8 ቁጥር 230 2026-05-22 ግዮን መጽሔት ቅጽ 8 ቁጥር 229 2026-05-04 ግዮን መጽሔት ቅጽ 7 ቁጥር 228 2026-04-21 ግዮን መጽሔት ቅጽ 7 ቁጥር 227 2026-03-06 በብዛት የተነበቡ አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ ተጨማሪ ጽሑፎችተመሳሳይ አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ ግዮን መጽሔት - 2026-06-13 በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች... የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ ግዮን መጽሔት - 2026-06-13 ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት... ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ ግዮን መጽሔት - 2026-06-13 በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት... ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ ግዮን መጽሔት - 2026-06-13 ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...