ቱርክ በሶማሊያ የመጀመሪያውን የባህር ላይ የነዳጅ ቁፋሮ ልትጀምር ነው

Date:

በሶማሊያ ታሪክ የመጀመሪያው የሆነውን የባህር ላይ የነዳጅ ቁፋሮ ፕሮጀክት ለመጀመር የሚያስችል የቱርክ የቁፋሮ መርከብ ዓርብ ዕለት በሞቃዲሹ ወደብ መድረሱ ተገልጿል።

ቻግሪ ቤይ የተሰኘችውና የቱርክን ሰንደቅ ዓላማ ያነገበችው ይህች ግዙፍ መርከብ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል በ2024 የተፈረመውን የሃይድሮካርቦን ልማት ስምምነት ተፈጻሚ ለማድረግ የመጣች ሲሆን፤ ስምምነቱ ለቱርክ የመንግሥት የነዳጅ ኩባንያ እያንዳንዳቸው 5,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ባላቸው ሦስት የባህር ክልሎች ላይ የፍለጋ እና የቁፋሮ መብት ይሰጣል።

በ2024 መጨረሻ ላይ በተካሄደው የሴይስሚክ ጥናት መሠረት የሚከናወነው ይህ ሥራ፣ ለሶማሊያ የመጀመሪያው የባህር ላይ ቁፋሮ ሲሆን ለቱርክ ደግሞ ከራሷ የባህር ክልል ውጪ የምታካሂደው የመጀመሪያው ጥልቅ ባህር ላይ የሚደረግ የቁፋሮ እንቅስቃሴ ነው።

የቱርክ ኢነርጂ ሚኒስትር አልፓርስላን ባይራክታር እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በተገኙበት በሞቃዲሹ ወደብ የክብር ሥነ-ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን፣ ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ወደ አዲስ የኃይል ልማት ምዕራፍ የሚያሸጋግር መሆኑ ተመልክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...