የግብፅ በኤርትራ ውስጥ ለሚከናወኑ የኢንዱስትሪ እና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የሚውሉ የቴክኒክ ባለሙያዎችን ለማሰማራት እና ዝርዝር የአዋጭነት ጥናቶችን ለማካሄድ መዘጋጀቷን አስታወቀች።
ይህ የተነገረው የግብፅ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ካሊድ ሀሺም ከኤርትራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር በካይሮ ባደረጉት ስብሰባ ወቅት ነዉ።
ሚኒስትር ካሊድ ሀሺም እንደገለጹት፣ ግብፅ ያላትን የኢንዱስትሪ ልምድ ለኤርትራ በማካፈል በአገሪቱ ስልታዊ የሆኑ ፋብሪካዎች እና የመሠረተ ልማት አውታሮች እንዲገነቡ ድጋፍ ታደርጋለች።
በተጨማሪም ግብፅ በኤርትራ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ማዕከላትን በመገንባት የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እንቅፋቶች በመቅረፍ ረገድ የበኩሏን ድርሻ ለመወጣት ተስማምታለች።
ይህም በቀይ ባሕር ቀጣና ያለውን ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ትስስር ለማጠናከር አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ይጠበቃል።
