ቱሪዝሙን ለማሳደግ አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ

Date:

የቱሪዝም ዘረፉን ለማሳደግ እና ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር የሚችል ለማድረግ ለአስጎብኝ ድርጅቶች አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ፡፡ የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት “በኢትዮጵያ ያለው የቱሪዝም አስጎብኝዎች ዘርፍ እድልና ተግዳሮቶች” ዙሪያ ከኢትዮጵያ አስጎብኝ ድርጅቶች ማህበር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል። የኢትዮጵያ አስጎብኝ ድርጅቶች ማህበር ፕሬዝዳንት አንድነት ፈለቀ ከዚህ ቀደም የቱሪዝም ዘርፍ ብዙም ትኩረት ያልተሰጠው እንደነበር ጠቁመው አሁን ላይ መንግሥት ቱሪዝሙን ለማሳደግና የኢኮኖሚ አቅም እንዲኾን ከማድረግ ጀምሮ ሌሎች እየሰራቸው የሚገኙ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸውል ብለዋል። ቱሪዝሙን ለማሳደግ እና ለወጣቶች የሥራ እድል መፍጠር የሚችል ለማድረግ ለአስጎብኝ ድርጅቶች አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስና የኑሮ ውድነት እንዲሁም በሀገር ውስጥ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ቱሪዝሙን እንደጎዳው አንስተው መንግሥት ሕጋዊ የኾነውን የአስጎብኝ ድርጅት ለማበረታታት ሕገወጦችን መቆጣጠርና የሚወጡ ሕጎችን ተግባራዊ ማድረግ አለበት ሲሉም ተናግረዋል።

ቀዳሚ ጽሑፍ
ቀጣይ ጥሑፍ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...