በታቦተ ህግ ላይ በመሳለቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክብር የሚነካ ቪዲዮ ያሰራጨ ግለሰብ በእስር ተቀጣ

Date:

የጥምቀትን በዓልን ምክንያት በማድረግ በታቦተ ህግ ላይ በመሳለቅ በቲክቶክ ያሰራጨ ግለሰብ በ1 ዓመት ከ4 ወር ቀላል እስር እንዲቀጣ መወሰኑን የወላይታ ዞን አረካ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ፖሊስ እንደገለፀው ወንጀሉን ከፈፀሙ ግለሰቦች መካከል በቀን 25/05/2017 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውሎ በህግ ጥላ ስር የቆየው ወጣት አቤል አዳፍሬ ነዋሪነቱ በአረካ ከተማ አረዳ ቀበሌ አስተዳደር ውስጥ ሲሆን በማህበራዊ ትስስር ገፅ ለተከታዮቹ ባጋራው የቲክቶክ ቪዲዮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክብር የሚነካ የእምነቱ ተከታዮችንም ያስቆጣ ተግባር መፈጸሙ ተገልፆአል።

ፖሊስ የተከሳሹን የምርመራ ሂደቱን ጨርሶ ወደ አቃቤ ህግ በማስተላለፍ አቃቤ ህግ በመሰረተው ክስ ተከሳሹ በተከሰሰበት የወንጀል ህግ ጥፋተኛ በመሆኑ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው ፍርድ ቤት በተከሳሹ ላይ ያስተምራል ያለውን በ 1 አመት ከ 4 ወር ቀላል እሥራት እንዲቀጣ መወሰኑን የዘገበው የከተማዋ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...