ዓሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ምንም አይነት ሕጋዊ እውቅና የለዉም

Date:

ዓሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ/ዓዴፓ/ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምንም አይነት ጊዜያዊም ሆነ ቋሚ ሕጋዊ እውቅና እና የምዝገባ ፈቃድ ያልወሰደ እና እና የምዝገባ ሂደቱን ያልጨረሰ ያልጨረሰ በመሆኑ፤ ሕብረተሰቡ ይህን ተረድቶ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ቦርዱ አሳስቧል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ፓርቲውን በተመለከተ የሰጠውን ውሳኔ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም እነ ዶሪ አስገዶም ዓሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ/ዓዴፓ/ በሚል ስያሜ በ26/2/2012 ዓ.ም የክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ ሕጋዊ የእውቅና ጥያቄ ለቦርዱ አቅርበው በምዝገባ ሂደት ላይ እንደነበሩ አስታውሷል፡፡

የፓርቲው ሕጋዊ የእውቅና ፈቃድ ሂደት በአገሪቱ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ ቆይቶ በኋላ፤ እነ ሐጎስ ወልዱ በቁጥር ዓዴ-0027/15 በቀን 25/07/2015 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ተቋርጦ የነበረው ሂደት እንዲቀጥል በማለት ማመልከታቸውን አስታውቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በድጋሚ በቁጥር ዓዴ-0032/15 በቀን 16/09/2015 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ጊዜያዊ የእውቅና ፈቃድ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ቦርዱ ገልጿል፡፡

ቦርዱም በሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ዓሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የተባለ ክልላዊ ፓርቲ ለመመስረት በ26/2/2012 ዓ.ም ለቦርዱ ጥያቄ አቅርበው የነበረው እነ አቶ ዶሪ አስገዶም መሆናቸውን እና በወቅቱ ከቀረበው የመስራች አባላት ዝርዝር ውስጥ እነ አቶ ሐጎስ ወልዱ ባለመኖራቸው እና ‘የዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አደራጅ ኮሚቴ ባልሆኑበት ሁኔታ የፓርቲ ምዝገባ ሂደቱን ለማስቀጠል የሚጠይቁበት አግባብ የለም’ በማለት ውሳኔ መስጠቱን አስታውሷል፡፡

ቦርዱ በሰጠው ውሳኔ ላይ እነ አቶ ሐጎስ ወልዱ በቀን 5/12/2015 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ‘የዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መስራች አባላት አይደላችሁም’ በማለት ጥያቄው ተቀባይነት የለውም መባሉ አግባብ አለመሆኑን ጠቅሰው፤ የውሳኔ ማስተካከያ እንዲደረግላቸው መጠየቃቸውን አመላክቷል፡፡

ይህን ተከትሎም ቦርዱ በድጋሚ በቁጥር አ1162/11/1372 መስከረም 08/2016 ዓ.ም ‘የቀድሞውን ውሳኔ ሊያስቀይር የሚችል ምክንያት አልተገኘም’ በማለት ውሳኔውን አጽንቶታል፡፡

በመቀጠልም እነ ዶሪ አስገዶም በቁጥር Adp0079/16 በቀን 11/01/2016 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ በአሁኑ ሰአት የተሻለ ሰላም በመኖሩ የተቋረጠው ሂደት እንዲቀጥል እና ሕጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ቦርዱም ፓርቲው የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት ጳጉሜ 4 ቀን 2012 ዓ.ም በትግራይ ክልል ባካሄደው ሕገ ወጥ ምርጫ የተሳተፈ በመሆኑ፤ ሕዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም ከቦርዱ በተጻፈ ደብዳቤ ማንኛውም አባላቸው የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በሕግ የተጣለበትን በሀገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱም ሆነ በፖለቲካ ፓርቲነት ለመመዝገብ የሚደራጅን አካል የመመዝገብ፣ የመቆጣጠር እና የመደገፍ ስልጣን በተመለከተ ግልጽ አቋሙን እንዲያሳውቅ መጠየቁ ተመላክቷል፡፡

በዚህም መሰረት በቁጥር 0073/16 በቀን 12/03/2016 ዓ.ም በተጻፈ መልስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በሕግ የተጣለበትን በሀገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱም ሆነ በፖለቲካ ፓርቲነት ለመመዝገብ የሚደራጅን አካል ለመመዝገብ፣ ለመቆጣጠር እና ለመደገፍ የተሰጠውን ስልጣን ተቀብለው እንደሚንቀሳቀሱ መግለጻቸውን አስታውቋል፡፡

ቦርዱም ሕዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የፓርቲው የምዝገባ ሂደት እንዲቀጥል፣ አደራጅ ኮሚቴው ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ያደረገው መስራች ጉባኤ ላይ የቦርዱ ተወካዮች እንዲገኙ ባለማሳወቁ በጉባኤው የተካሄዱ የአመራር ምርጫም ሆነ በጉባኤው የተወሰኑ ውሳኔዎች ያልተመዘገቡ መሆኑን ገልጿል፡፡

እንዲሁም አደራጅ ኮሚቴው ጉባኤ ከመካሄዱ 30 ቀናት አስቀድሞ ቦርዱ ታዛቢ እንዲመድብለት እንዲያሳውቅ እና ረቂቅ የፓርቲውን ደንብ፣ ፕሮግራም እና እና መመስረቻ ጽሁፍ ለቦርዱ በማቅረብ መስራች ጉባኤውን በድጋሚ እንዲያካሂድ መወሰኑን አስታውሷል፡፡

ፓርቲው በቁጥር Adp0075/16 በቀን 14/05/2016 ዓ.ም የፓርቲው አባላት የሚገኙበት ኢሮብ ወረዳ ከግማሽ መሬት በላይ በኤርትራ ሠራዊት ቁጥጥር ስለሚገኝ በአካባቢው ተንቀሳቅሶ አባላት ማደራጀት ስለማይችል የኤርትራ ሠራዊት የተጠቀሱትን አካባቢዎች እስከሚለቅ እና የተዘጋው መንገድ እስከሚከፈት ድረስ ለጉባኤው በቂ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፓርቲው ከቦርዱ ምንም አይነት ጊዜያዊም ሆነ ቋሚ ሕጋዊ እውቅና እና የምዝገባ ፈቃድ ሳያገኝ በቦርዱ ሕጋዊ እውቅ እና ፍቃድ እንደተሰጠው በማስመሰል በተለያዩ መድረኮች አሳሳች መግለጫ እንደሚሰጥ ቦርዱ መረዳቱን ገልጿል፡፡

ቦርዱም በቀን 23/07/2017 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ፓርቲው የጀመረውን ሕጋዊ እውቅና የማግኘት ሂደት ቦርዱ እንዲያሟላ የጠየቃቸውን መስፈርቶች በራሱ ጊዜ ሳያሟላ አንጠልጥሎ ሳይጨርስ የቀረ መሆኑን አስታውቋል፡፡

እንዲሁም ፓርቲው የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ማሕበረሰቡን የሚያሳስቱና የሚያደናግሩ በመሆኑ፤ ፓርቲው ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምንም አይነት ጊዜያዊም ሆነ ቋሚ ሕጋዊ እውቅና እና የምዝገባ ፈቃድ ያልወሰደ እና እና የምዝገባ ሂደቱን ያልጨረሰ በመሆኑ ሕብረተሰቡ ይህን ተረድቶ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...