“በቻይና ላይ የተጣለው ታሪፍ ሊቀንስ ይችላል” ትራምፕ

Date:

በቻይና ላይ የተጣለው የ145 በመቶ ታሪፍ ሊቀንስ እንደሚችል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ።

የፕሬዝዳንቱን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በአሜሪካና ቻይና መካከል የተቀሰቀሰው የንግድ ጦርነት፤ ትልቅ የሚባል የታሪፍ መጠን እንዲጣል አድርጓል።

የሁለቱ ሀገራት ባለስልጣናት በስዊዘርላንድ ሌነጋገሩ ነው መባሉን ተከትሎ የተሰነዘረው የፕሬዝዳንቱ ንግግር፤ የንግድ ጦርነቱ መለሳለስ እያሳየ ስለመሆኑ ጠቋሚ ተደርጓል።

ትራምፕ ታሪፉ ከዚህ በላይ አይጨምርም፣ ይልቁንም እየቀነሰ መምጣቱ እንደማይቀር እናውቃለን ሲሉ መናገራቸውንም ቢቢሲ ዘግቧል።

ቻይና በአሜሪካ የተጣለባትን የ145 በመቶ ታሪፍ ተከትላ በአሜሪካ ምርቶች ላይ የ125 በመቶ ታሪፍ መጣሏ ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...