አሜሪካና ሳዑዲ አረቢያ የ600 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የንግድ ስምምነት 

Date:

አሜሪካና ሳዑዲ አረቢያ 600 ቢሊየን  የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ የንግድ ስምማነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን ዛሬ ለይፋዊ  የስራ ጉብኝት ሳዑዲ አረቢያ የገቡት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሳዑዲ አረቢያው አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን ናቸው የተፈራረሙት።

ስምምነቱ ሳዑዲ አረቢያ በዓለም የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዕከል ለመሆን ለያዘችው እቅድ አስፈላጊውን የቴክኖሎጂ ግብዓት ከአሜሪካ  የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ለማግኘት ያስችላታል።

የስምምነት ስነ-ስርዓቱን የአሜሪካ የቴክኖሎጂ አምራች ድርጅቶች  ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች በአካል ተገኝተው ታድመዋል።

ከቴክኖሎጂ ባለፈ አሜሪካ ለሳዑዲ አረቢያ የምታደርገውን የ142 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ስምምነቱ ያካትታል ተብሏል።

በዛሬው ዕለት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ያቀኑት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ በቀጣይ በወደ ኳታር እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በማቅናት በአጠቃላይ ከ1 ትሪሊዮን የአሜሪካ ዶላር  በላይ የሚሆን የንግድ ስምምነት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...