ክርስቲያኖ ጁኒየር ለፖርቹጋል የመጀመሪያ ጨዋታውን አደረገ

Date:

የፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ልጅ የሆነው ክርስቲያኖ ጁኒየር ለፖርቹጋል ከ15 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን በዛሬው ዕለት አድርጓል።

ክርስቲያኖ ጁኒየር የፖርቹጋል ከ15 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከጃፓን አቻው ጋር ባደረገው ጨዋታ አባቱ የሚታወቅበትን 7 ቁጥር ማልያ በመልበስ በ53ኛው ደቂቃ ተቀይሮ ገብቷል።

የክርስቲያኖ ሮናልዶ እናት ማሪያ ዶሎሬስ ዶስ ሳንቶስ በሜዳው ተገኝተው ልክ ለልጃቸው እንደሚያደርጉት ሁሉ ለልጅ ልጃቸውም ድጋፋቸውን አሳይተዋል።

በጨዋታው የፖርቹጋል ከ15 ዓመት በታች ብሔራዊ ጃፓን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ያሸነፈ ሲሆን ክርስቲያኖ ጁኒየር ግብ አላስቆጠረም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...