በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሸነን ዱጎ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 11 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የዞኑ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።
በተለምዶ አይሱዙ የተሰኘው የደረቅ ጭነት መኩና 42 ሰዎችን ከተለያዩ ሸቀጦች ጋር ጭኖ ከዋልዳያ ከተማ ወደ መሰላ ወረዳ በመጓዝ ላይ ሳለ በትላንትናው ዕለት ምሸት 2:30 ላይ ነው አደጋው የደረሰው።
መኪናው 42 ሰዎዎችን ከተለያዩ እቃዎች ጋር አብሮ ጭኖ የነበረ ሲሆን መስመሩን በመሳት ከ50 እስከ 70 ሜትር በሚርቅ ገደል ውስጥ የገባ ሲሆን በዚህም የ 11 ሰዎች ህይወት ማለፉ ነው የተገለጸው።
በአደጋው በተጨማሪም በ28 ሰዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በሂርና የመጀመሪያ ሆስፒታል እንዲሁም በጭሮ አጠቃላይ ሆስፒታል ክትትል እየተደረገላቸው ነው።
የአደጋው ምክንያትም የጥንቃቄ ጉድለትና ከአቅም በላይ መጫን መሆኑን የወረዳው የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ኢንስፔክተር ረቢራ አየለ ተናግረዋል።
