በአዋሽ ፈንታሌ በተከሰተው ርዕደ መሬት ምክንያት አደጋ እንዳይደርስባቸው በመስጋት መተሃራ አካባቢ ባሉ 7 ቀበሌዎች የሚኖሩ ከ32 ሺሕ 620 ነዋሪዎች አካባቢውን እንዲለቁ ተደርጎ እንደነበር፤ የኦሮሚያ ክልል ቡሳ ጎኖፋ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ኃላፊ ጥበቡ ኩምሳ ለአሐዱ ተናግረዋል።
በአሁን ሰዓት በአካባቢዎቹ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ስጋት ባለመኖሩ ምክንያት ነዋሪዎቹን ወደቀደመ መኖሪያ አካባቢያቸው የመመለስ ሥራ መጀመሩን አብራርተዋል።
ኃላፊው በተጨማሪም፤ “ተፈናቃዮቹ ከአካባቢያቸው ከተነሱ በኋላ ባሉት ሦስት ወራት የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ባለመኖሩ ነዋሪዎቹ ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ ተደርጓል” ብለዋል።
በአዋሽ ፈንታሌ መተሃራ ከተፈናቀሉት ከ32 ሺሕ 620 ሰዎች በተጨማሪ የመሬት መንቀጥቀጡ ጉዳት እንደማያደርስባቸው በመስጋት ተፈናቅለው በአፋር ክልል የሚገኙ ከ60 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች የሚገኙ ሲሆን፤ ተፋናቃዮቹ አሁን ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡
#አሐዱ ሬድዮ
