የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን ሦስት የዲጂታል መፍትሔዎች ይፋ ተደረጉ

Date:

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ኢትዮ ቴሌኮም የሀገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ስርዓትን፣ የተቀናጀ ነዳጅ ክፍያ ስርዓት እንዲሁም ሀገር አቀፍ የትራፊክ ቅጣት ማዕከላዊ አስተዳደር ስርዓትን የዲጂታል ሶሉሽኖችን ተግባራዊ አድርገዋል፡፡

እነዚህም በሀገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርትና በነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ ያሉ ዘልማዳዊ የአሰራር ሂደቶችን ለማዘመንና በነዳጅ አቅርቦትና ግብይት ረገድ ትክክለኛ መረጃ በወቅቱ ለማግኘት፣ ደንበኞች በተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት አማራጮች መጠቀም እንዲችሉ፣በትራፊክ ቅጣት አስተዳደር ግልጽነት ያለው አሰራርን ለማስፈንና የተገልጋዮችን እንግልት ለማስቀረት የላቀ ሚና ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡

በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረጉት የዲጂታል መፍትሔዎች ተከታዮቹ ናቸው፡-

1. የሀገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ስርዓት (Cross-Country Public Transport Service System)

ይህ የዲጂታል መፍትሔ አገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶችን ለማግኘት ያሉ የሥራ ሂደቶች በቀላሉ ለማስተዳደር እና ለማቀላጠፍ የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡

ትግበራው ከፈቃድ አሰጣጥ እና የሕግ ተገዥነት (Regulatory Compliance) ጀምሮ እስከ ትኬት መቁረጥ እና ዲጂታል ክፍያ ድረስ ወጥ የሆነ መፍትሔ ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዋና ዋና ተግባራቱም፤ “የሽያጭ እና የገቢ ሁኔታ ግልጽነትን ለማስፈን፣ በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችም ሆነ በተጓዦች ላይ ሊከሰት የሚችል ስርቆትንና ማጭበርበርን ለመከላከል፣ የመረጃ አያያዝን ለማዘመንና ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እንዲሁም ስለ አውቶቡስ እንቅስቃሴ፣ የትኬት ሽያጭ፣ የተሳፋሪ ብዛት እና የአገልግሎት ሽፋንን አስመልክቶ አስተማማኝ እና ቅጽበታዊ መረጃ ለማግኘት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው” ተብሏል፡፡

ነባሩን ማኑዋል/ወረቀት ተኮር የትራንስፖርት ስምሪት አሰራር የፍቃድና የምዝገባ ስርዓት፣ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ምዝገባና ስምሪትን እንዲሁም የማኑዋል ቲኬት ሕትመትና ክፍያዎችን ዲጂታል በማድረግ የአስተዳደር ወጪን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ተነግሯል።

2. የተቀናጀ ነዳጅ ክፍያ ስርዓት ሶሉሽን (Enabling All Payment Platforms for Fuel Payment)

ይህ የመፍትሔ ስርዓት ሁሉንም የፋይናንስ ተቋማት (ሁሉንም ባንኮች፣ ዋሌቶች፣ እና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን) ከማዕከላዊ የነዳጅ አስተዳደር ሥርዓት ጋር የሚያገናኝ አገር አቀፍ የተቀናጀ ነዳጅ አቅርቦት ስርዓት መፍትሔ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎች በቅንጅት እንዲሰሩና የነዳጅ ግብይቶችን አንድ ወጥ በሆነ አሰራር በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመፈጸም የሚያስችል መፍትሔ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ለትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ለነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ቅጽበታዊ ሪፖርቶችን ለማግኘት፣ የተሻለ የገበያ ቁጥጥር ለማስፈን፣ የአገር አቀፍ የነዳጅ ክምችትን፣ ሥርጭትን እና ሽያጭን በቅርበት በመከታተል ሕገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን በመቅረፍ ግልጽነት እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ለመስጠት ጠቀሜታው የላቀ ነው ተብሏል፡፡

3. ሀገር አቀፍ የትራፊክ ቅጣት ማዕከላዊ አስተዳደር ስርዓት (National Traffic Point – Based Penalty Management System)

በሀገር አቀፍ ደረጃ የትራፊክ ሕጎች በተገቢው መንገድ እንዲተገበሩ የሚረዳ ሲሆን፣ በዲጂታል የታገዘ የትራፊክ ቅጣት አስተዳደርን በማስፈን፣ በማዕከል ደረጃ ዳታ የሚመዘገብበትና በሀገር አቀፍ ደረጃ አንድ ወጥ የሆነ የትራፊክ አስተዳደር ለማስፈን የሚያስችል አሰራር መሆኑ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ ያለውን ማኑዋል የትራፊክ ቅጣት አሰራርን በሀገር አቀፍ ደረጃ ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል ለመቀየር እንዲሁም የዲጂታል መዝገብ፣ የተማከለ የትራፊክ ቅጣት ስርዓት፣ የትራፊክ የቅጣት ነጥብ አያያዝ፣ ቅጣቱን ለመፈጸም ያለው ምቹነት፣ ዳታን በመተንተን የመረጃ ውስንነትን እና ውጤታማ ያልሆነ የሀብት አጠቃቀምን ለመቅረፍና ፖሊሲዎችን ለማውጣት የመረጃ እጥረት ተግዳሮቶችን ለመፍታት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

በተጨማሪም በሀገሪቱ የሚገኙ የአሽከርካሪዎችን ሙሉ መረጃዎችን በመመዝገብ፣ የትራፊክ ሕግ ጥሰቶችን ለመቆጣጠር እንዲሁም ጤናማ የትራፊክ ፍሰትን እውን ለማድረግ እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡

ተግባራዊ የተደረጉት መፍትሔዎች በግል ሶፍትዌር አልሚ ተቋማት የለማ ሲሆን፤ እንዲሁም የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት አማራጮች ከኢትዮ ቴሌኮም ሥርዓቶችና ከቴሌብር ጋር በኤፒአይ (API) በቀላሉ እንዲዋሀዱ በማድረግ፣ የጋራ የመሥራት አቅምን (interoperability) በማሳደግ የሥራ ፈጠራንና አካታች የዲጂታል ሥነ-ምህዳርን ማጠናከር የቻለ መሆኑ ተገልጿል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...

ከ 50 ሚሊዮን በላይ መራጮች በማንዋልና በዲጂታል ተመዝግበዋል

ከየካቲት 28_መጋቢት 28 የመራጮች ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበር ይታወቃል። በተለያዩ ጉዳዮች...