የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለመቄዶንያ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

Date:

የፌዴራል ቤቶች ኮርሬሽ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንዲሁም፤ ፒያሳ አካባቢ ለሚገኝ አንድ የንግድ ቤት በዛሬው ዕለት ድጋፍ አድርጎል።

በመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ውስጥ ምንም ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው 8 ሺሕ 500 በላይ ተረጂዎችን በመረዳት ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ በጎ አድራጎት ድርጅቱ በቀን 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ለተረጂዎች እንደሚያወጣ ተገልጿል።

መቄዶንያ በአጠቃላይ በ46 ከተሞች ቅርንጫፍ በመክፈት ሥራውን በከፍተኛ ሁኔታ በማስፋፋት ላይ እንደሚገኝም የበጎ አድራጎት ድርጀቱ ረዳት ዋና ሥራ አስኪያጅ እሌኒ ገ/እየሱስ ተ/ሃይማኖት ተናግረዋል።

በቀጣይ በአዳዲስ ከተሞች ላይ እንደሚከፍት ገልጸው፤ በመቂ፣ ወሊሶ፣ ሱሉልታ፣ ሰበታ፣ ደብረብርሃን፣ ሆሳዕና፣ ዲላ እና በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ለመስራት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የመቄዶንያ አጠቃላይ ድርጅቱን በቀጣይ 250 ለማድረስ እየሰራ ይገኛልም ተብሏል።

በድርጅቱ ውስጥ 3 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ተረጂዎች፤ እራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ የማይችሉ እና ዳይፕር ተጠቃሚ እንደሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም በተቋሙ ከ2 ሺሕ በላይ የአእምሮ ሕሙማን እንደሚገኙ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...