በምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ተከፈተ

Date:

“ኢቴክስ  2025 ” የተሰኘ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት አዘጋጅነት በዛሬው እለት ተከፍቷል ።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር  ትግስት ሃሚድ ፤ፈጠራን እና የድጅታል እድገትን የሚያፋጥነውን ኢቴክስ 2025 በማዘጋጀታችን ደስተኞች ነን ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ ይህ ኩነት የኢትዮጵያን የድጅታል ራዕይ በማሳደግ በኩል  ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል።

ኤክስፖው የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ አቅምን ለማስተዋወቅ እና ለማሳደግ እንዲሁም በዚህ ዘርፍ ላይ ከተሰማሩ አለም አቀፍ ሀገራት ጋር ትስስር ለመፍጠር ያግዛልም ብለዋል።

ኤክስፖ አለም የሳይበር ወንጀልን ለመከላከል እያደረገ ባለው ጥረት ላይ ኢትዮጵያ ቁልፍ ተዋናይ እንድትሆን እንዲሁም በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ ጥረቶችን ለአለም ለማሳየት ይረዳል ተብሏል።

የቴክኖሎጂ ኤክስፖው ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች የሚሳተፉበት ሲሆን ተሳታፊዎቹ ከተለያዩ 45 ዓለም ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸው ተሰምቷል።

እንደ ሜታ፣ ሁአዌና ኖኪያ የመሳሰሉ ግዙፍ ዓለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያችና  መሪዎች  የዚህ ኤክስፖ አካል ናቸው።

በዛሬው እለት በተከፈተው ኢቴክስ 2025 ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ስላሴን ጨምሮ የፖሊሲ አውጪዎች፣በዘርፉ ላይ ያሉ ሙሁራን፣ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች፣ኢንቬስተሮች ተገኝተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...