ማንኛውም የዳኝነት አገልግሎት መስጠት አቁመናል (የመቐለ ፍርድ ቤት)

Date:

ትላንት ግንቦት 12 /2017 ዓ.ም በመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ደጃፍ የተለጠፈው ማስታወቂያ፥ ” በላያችን ላይ ያንዣበበው የደህንነት ስጋት መፍትሄ እስኪበጅለት ድረስ የመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ጨምሮ በሰባቱ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ዳኞችና ፍርድ ቤቶች ለጊዜው ማንኛውም የዳኝነት አገልግሎት መስጠት አቁመዋል ” ይላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የማስታወቂያውን ትክክለኝነት ለማረጋገጥ ሐውልት ፣ ዓይደር ፣ ቀዳማይ ወያነ ወደ ተባሉ ክፍለ ከተሞች ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

በዚህም ማንኛውም አይነት አገልግሎት መቆሙን አረጋግጧል።

ዛሬ ከሰዓት በኋላ ደግሞ የክልሉ ጊዚያዊ  አስተዳደር ፍርድ ቤቶቹ መዘጋታቸው አረጋግጦ ለመዝጋታቸው ምክንያት የሆነ ችግር አጣርቶ እርምጃ እንደሚወስድ ቃል ገብቶ ዳኞቹ ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ተማፅኗል።

ለመሆኑ ፍርድ ቤቶቹ እስከ ስራ ማቆም እርምጃ እንዲወስዱ የገፋፋቸው ምክንያት ምንድን ነው ?   

ባለፈው አርብ ግንቦት 8/2017 ዓ.ም በመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ዘውዱ የተባለች ሟች ላይ የተፈፀመ ወንጀል ለመዳኘት በተጠራው ችሎት ላይ የበዳይ ተጠርጣሪ ቤተሰቦች ችሎቱ ከመረበሽ በዘለለ በዳኞችና አቃቤ ህግ ላይ መጥፎ ቃላት በመጠቀም ዝተዋል።

በረብሻው ምክንያትም በዛው ቀን በተጠርጣሪዎች ላይ ሊሰጥ የነበረው የመጨረሻ ውሳኔ ተሰርዞ ለግንቦት 18/2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቆጠሮ ተይዘዋል።   

ይህንንና ሌሎች ስጋቶች ” አላሰራ ብለውኛል ” ያለው የትግራይ ዳኞች ማህበር በፍትህ አረጋጋጭ ዳኞች ላይ የሚታዩ ችግሮች ካልተፈቱ እስከ ስራ ማቆም የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ ግንቦት 9/2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አሳውቆ ነበር።

ይህንን ተከትሎ ዛሬ ግንቦት 12/2017 ዓ.ም የስራ ማቆም እርምጃ ወስዷል። እርምጃው የጀመረበት እንጂ የሚቆምበት ቀን አልተገለፀም።

ዳኞችና ፍርድ ቤት ለጠሩት ስራ የማቆም አድማ ምክንያት የሆነው ችግር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚፈታ የገለፀው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ዳኞች የህዝባዊ አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ በማመፀን የተፈጠረው ችግር በአስቸኳይ አጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...