በመንግሥት ብቻ ሲሰጥ የነበረው የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት የግል ዘርፍን ጨምሮ ሌሎች አካላት እንዲሳተፉ የሚያስችለው ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መተላለፉን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አስታወቀ።
በሀገሪቱ ባለፉት ዓመታት የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት በመንግሥት ብቻ ሲሰጥ መቆየቱን ያስታወሰው ምክር ቤቱ ከዘርፉ እያደገ ከመጣው ፍላጎት አንፃር መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የግል ዘርፉን የሕብረት ሥራ ማሕበራትንና የሙያ ማሕበራትን ማሳተፍ የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝቧል።
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በሙሉ ድምጽ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 45ኛ መደበኛ ስብሰባው በበርካታ ጉዳዮች ላይ ከተወያየ በኋላ ውሳኔ ያሳለፈው ምክርቤቱ የስርዓተ ምህዳር አገልግሎት ክፍያ ረቂቅ አዋጅን በተጨማሪነት ለፓርላማው እንዲተላለፍ መወሰኑ ካፒታል ለመረዳት ተችሏል።
#capitalethiopia
