የትራምፕ አስተዳደር ሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን እንዳይቀበል ያገደ ሲሆን ይህም ከአሜሪካ አንጋፋው ዩኒቨርስቲ ጋር ያለውን አለመግባባት አባብሶታል።
የአገር ውስጥ ደህንነት መስርያ ቤት ኃላፊ ክሪስቲ ኖኤም በኤክስ ገጻቸው ላይ እንደጻፉት አስተዳደሩ ሀርቫርድ “ተማሪዎች እና ስደተኛ ያልሆኑ ተማሪዎችን መቀበል የሚያስችለውን ዕድል ሕግን ማክበር ባለመቻሉ ምክንያት ተሰርዟል” ብለዋል።
“ይህ በመላው አገሪቱ ለሚገኙ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች እና የትምህርት ተቋማት እንደ ማስጠንቀቅያ ይሁናቸው” ሲሉ ሐሙስ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ልጥፍ ላይ ጽፈዋል።
ሀርቫርድ ውሳኔውን “ሕገ ወጥ” ሲል በመግለጫው አውግዞታል።
“ከ140 በላይ አገራት የመጡ እና ዩኒቨርሲቲውን እና ይህችን አገር በማይተመን መልኩ የሚያበለጽጉትን ዓለም አቀፍ ተማሪዎቻችንን እና ምሁራኖቻችንን ለማስተናገድ ሙሉ በሙሉ ቁርጠኞች ነን” ሲል ዩኒቨርሲቲው በመግለጫው ላይ ምላሽ ሰጥቷል።
