3ኛው ዙር የትግራይ ሀገር አቀፍየኢንዱስትሪ ኤክስፖ “የኢንዱስትሪ ኤክስፖ ለትግራይ ዳግም ግንባታ” በሚል መሪ ሃሳብ እንደሚካሄድ የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ገልጿል።
በኢንዱስትሪ አውደ ርዕዩ ላይ በማምረቻው፣ ግብርና ማቀነባበር፣ በግብርና፣በማዕድን ግብአት፣ በፋይናንስ አገልገሎት እና ሌሎች ዘርፎች ላይ የተሰማሩ 150 የሚደርሱ አምራቾች ምርታቶቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።
በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት ትግራይ ክልል በምን ያህል ወደኋላ እንደተመለሰ ለተቀረው ማህበረሰብ ለማሳየት እና ምን ያህል የተቀናጀ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚያስፈልግ ለማስገንዘብ እንደሚያግዝ ተነግሯል።
ኤክስፖው ከሰኔ 28 እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በመቐለ ከተማይካሄዳል።
ኤክስፖውን ያዘጋጁት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የትግራይ ክልል የኢንዱስትሪ ቢሮ እና የትግራይ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በጋራ በመሆን ነው ተብሏል።
