ፖርት ሱዳን-የሱዳን ጦርነት አካባቢዉን እያዳረሰ ነዉ

Date:

የሱዳን መከላከያ ጦር የሊቢያ የጦር አበጋዝ ኸሊፋ ሐፍጣር የሚያዙት ሚሊሺያ ጦር ጥቃት እንደከፈተበት አስታወቀ።

የሱዳን መከለከያ ጦር አዛዦች እንደሚሉት ሱዳንን ከሊቢያና ከግብፅ ጋር በሚያዋስነዉ ድንበር ላይ የሠፈረዉ ጦራቸዉ በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦርና በኸሊፋ ሐፍጣር ኃይላት የተቀናጀ ጥቃት ተከፍቶበታል።

ሶስት ማዕዘናማዉ አካባቢ ሠፍሮ የነበረዉ የሱዳን መከላከያ ጦር ዳግም ለመደራጀት ከአካባቢዉ ማፈግፈጉን አዛዦቹ አስታዉቀዋል።

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ለረጅም ጊዜ ከከበባት ከአል ፋሻር ከተማ በመቶዎች ኪሎ ሜትር  ርቀት ላይ በሚገኘዉ ድንበር ሠፍሮ የነበረዉ ጦር በአብዛኛዉ ከቀድሞ አማፂ ኃይላት ተዋጊዎች የተዉጣጣ ነዉ።

የሐፍጣርና የፈጥኖ ደራሹ ኃይላት የድንበሩን መተላለፊያ፣ ጦር መሳሪያ ለማሻገር ይጠቀሙበታል በማለትም የሱዳን መከላከያ ጦር ይወቅሳል የሐፍጣር ኃይል ግን ወቀሳዉን አስተባብሏል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ራሳቸዉን ፊልድ ማርሻል ብለዉ ለሚጠሩት ኸሊፋ ሐፍጣር ከፍተኛ ድጋፍ ከሚሰጡ መንግሥታት አንዷ ናት።

የሱዳን መከላከያ ጦር ደግሞ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦርን ትረዳለች በማለት በተደጋጋሚ ይወቅሳል።

dw amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...