ሰሜን ኮሪያ በርካታ ሮኬቶችን ማስወንጨፏን የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሮኬቶቹ ከፒዮንግያንግ አቅራቢያ ሱና አካባቢ የተወነጨፉ መሆናቸውን የኮሪያ እና አሜሪካ የስለላ ቡድኖች ገልጸው፤ ዝርዝር መረጃ እያፈላለጉ መሆናውን ተናግረዋል፡፡
ሰሜን ኮሪያ ትንኮሳዋን የማታቆም ከሆነ ጥምር ሀይሉ አስፈላጊውን ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቱን የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡
የደቡብ ኮሪያ መገናና ብዙሀን ዮንሀፕ ሮኬቶቹ ከቢጫ ባህር መወንጨፋቸውን መዘገቡን ኤቢሲ ኒውስ ነው ያስነበበው ፡፡
