አሜሪካ በ6 ወር አንዴ የሚወሰደውን የኤች አይ ቪ መከላከያ ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቀደች።
ሌናካፓሺር (Lenacapavir) የተሰኘው የ ኤች አይ ቪ (HIV) መከላከያ የሆነው መድኃኒት በአሜሪካው ምግብና መድኃኒት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ አግኝቷል።
በሙከራ ደረጃ 99 በመቶ ኤች አይቪን የመከላከል አቅም አለው የተባለው መድኃኒቱ በመርፌ መልክ የሚሰጥ ነው።
ከዚህ ቀደም በየቀኑ የሚወሰድ እንክብል እንዲሁም በየ 2ወሩ በመርፌ የሚሰጥ የጸረ ኤች አይቪ ኤድስ መድኃኒት ገቢያ ላይ የነበረ ሲሆን ይህ የሚለየው የመውሰጃውን ጊዜ ወደ 6 ወር በማሳደጉ ነው።
በምርምር ወቅት ከአፍሪካ ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ዜጎችን ማሳተፍ ችሏል የተባለው ይኸው መድኃኒት በዘርፉ ትልቅ ውጤት የተመዘገበበት ነው ተብሏል።
ምንም እንኳን ውጤታማ ቢሆን ዋጋው ውድ መሆኑ ስጋት ፈጥሯል።
መድኃኒቱ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎችን የሚያድን ሳይሆን ተጋላጭ የሆኑ ግለሰቦች በቫይረሱ እንዳይያዙ የሚከላከል Pre-Exposure Prophylaxis (PrEP)ነው።
