አንዳንድ ነገሮች

ከባቢሎን ምርኮ እስከ ቤተልሔም ኮከብ

ኢራን እና አይሁድ ምንና ምን ናቸው? በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ፤ ግዮን መጽሔት :- በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ከ72ቱ አርድዕት መካከል የሚመደበው ወንጌላዊው ሉቃስ- በመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ዘንድ፤ ‹‹ባለመድኃኒቱ/ሐኪሙ እና የታሪክ አዋቂው›› ቅዱስ ሉቃስ በስሙ የተመዘገበለትን የሉቃስ...

አደይ ኢትዮጵያ ጓል አስመራ…!!

የቀድሞ ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የስንብት ቃል ለጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ አሕመድ!! በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) 1.  እንደ መንደርደሪያ ግዮን መጽሔት :- የቀድሞ የሀገራችን ፕሬዚደንት የነበሩት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የፕሬዝደትነት ጊዜያቸውን ካጠናቀቁ በኋላ አብዛኛው ጊዜያቸውን ‹‹በዕርቀ-ሰላም እና በአረንጓዴ ልማት›› ሥራ ዙሪያ ባዋሉበት ወቅት፤ ለተደጋጋሚ ጊዜያት ከክቡርነታቸው ጋር ለመገናኘትና ረዘም ያለ የቃለ-መጠይቅ ቆይታ ለማድረግ ዕድሉ ገጥሞኝ ነበር፡፡ ከፕ/ት ግርማ ጋር ቆይታ ለማድረግ ምክንያት የሆነኝ ደግሞ ክቡርነታቸው ከርእሰ ብሔርነት ሥራቸው በኋላም የቀጠሉበት ‹የሰላም እና የአረንጓዴ ልማት› አጀንዳዎች ነበሩ፡፡ እናም እርሳቸው በሰላም እና በአረንጓዴ ልማት ላይ እያከናወኑ ያሉትን ሥራዎቻቸውን በተመለከተ ለ94ኛ ዓመታቸው መታሰቢያ የሚሆን ፈረንጆቹ ‹‹Coffee Table Magazine›› በሚል የሚጠሩት ዓይነት ሥራቸውን የሚዘክር መጽሔት ለማዘጋጀት ኃላፊነት ወስጄ ስሠራ ነበር፡፡ ፕ/ት ግርማ ከርእሰ ብሔርነት ኃላፊነታቸው መጠናቀቅ በኋላም በተለይ በሰላም እና በአረንጓዴ ልማት ዙሪያ ሰፊ እንቅስቃሴያቸውን አጠናክረው አስቀጥለውት ነበር፡፡ እርሳቸው የደን/የአረንጓዴ ልማት ጉዳይ እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ ዋንኛ አጀንዳቸው ነበር፡፡ እንደውም ታሪክ እንደሚነግረን፤ መ/አ ግርማ በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን የፓርላማ አባል በነበሩበት ጊዜ በሀገሪቱ ‹‹የደን ሕግ›› እንዲወጣ ያደረጉ የአረንጓዴ ልማት ጠበቃ፤ የተፈጥሮ/የአካባቢ ጥበቃ ተቆራቋሪ ጀግና ነበሩ፡፡  ለክቡርነታቸው ከተፈጥሮ እኩል ለእርሳቸው የሰላም ጉዳይም ዋንኛና ተቀዳሚ አጀንዳቸው ነበር፡፡ ፕ/ት ግርማ፤ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ዕርቀ-ሰላም ይወርድ ዘንድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች፤ ከእነ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ ቀዳሚ ሙፍቲ ኻጂ እንድሪስ፣ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ክ አባትና መሪ ከሆኑት ከብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ፣ ከወንጌላውያን አብያተ-ክርስቲያናት አባቶች፣ በኢትዮጵያና በወጪ አገራት ከሚኖሩ ኤርትራውያን ምሁራን፣ ከአገር ሽማግሌዎች፤ ከእናቶች፣ ከአባ ገዳዎች… ወዘተ. ጋር በመሆን በብዙ ለፍተዋል፤ ደክመዋል፡፡ ፕ/ት ግርማ ዕድለኛ ነበሩ፡፡ ፈጣሪ ዕድሜያቸውን አርዝሞላቸው በሕይወት እያሉ በብዙ የደከሙበት፤ የለፉበት የዕርቀ-ሰላም፣ የአረንጓዴ ልማት አጀንዳ ዕውን ሆኖ ለማየት በቁ፡፡ እናም በጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥረትና በጎ ፈቃድ የተነሳ ለሦስት ተከፍለው (የሀገር ቤቱ፣ ሕጋዊው እና ገለልተኛ) የነበሩትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ አባቶች ዕርቀ-ሰላም ለማየት ቻሉ፡፡ ክቡርነታቸው ለዕርቀ-ሰላሙ ስኬት በመኖሪያ ቤታቸውም ከሁለት ዐሥርተ ዓመታት በላይ በስደት አሜሪካ አገር ለኖሩት ለፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ እና አብረዋቸው ከስደት ለተመለሱት ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት/አባቶች፤ ‹የእንኳን ደህና መጣችሁ!› አቀባባልና የምሳ ግብዣ አድርገውላቸው ነበር፡፡ በመቀጠልም፤ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ዕርቀ-ሰላም እንዲወርድ ያደረጉት ጥረት ፍሬ አፍርቶ በጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት፤ ከሁለት ዐሥርት ዓመታት በላይ የዘለቀውን ቁርሾ በዕርቀ-ሰላም እንዲደመደም አደረጉ፡፡ በአዲስ አበባና በአስመራ ከተማ ጎዳናዎች በዘንባባ ዝንጣፊና በነጭ ርግብ ሲደምቁ፤ በኢትዮጵያውያንና በኤርትራውያን ወንድማማችና እኅትማማች ሕዝቦች የናፍቆትና የስስት እንባ የአስመራና አዲስ አበባ ጎዳናዎችን በደስታና በአንድነት ሲቃ ተውጠው ሲያነቡ - ይህን ብዙዎቻችንን ያስደሰተና ያስገረመ ታሪካዊ ትእይንት ክቡር ፕሬዚደንት በዓይናቸው ዐይተው፤ በጆሮአቸው ሰምተው በደስታ እንባቸውን አፍሰዋል፡፡  ፕ/ት ግርማ ይህን እርሳቸውና የሰላም አፍቃሪ ኢትዮጵያውያን ወዳጆቻቸው ምኞት ተሳክቶ በማየታቸው በአካል እና በደብዳቤ ጭምር ለጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) የምስጋና የደስታ መግለጫ ቃል ልከው ነበር፡፡ 2.  የፕ/ት ግርማ የመጨረሻ ቃል ለጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ አሕመድ  ክቡርነታቸው ለዚህ ታላቅ ታሪካዊ ክስትት የተሰማቸውን ደስታ ለመግለጽ በማሰብ ለክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የተላከውን ደብዳቤ የማርቀቅ ሥራ ኃላፊነቱን ለእኔ ነበር የሰጡኝ፡፡ ክቡርነታቸው በሰጡኝ ኃላፊነትና መመሪያ መሠረትም ለክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ አሕመድ የሚላከውን ደብዳቤ በጥንቃቄ አዘጋጅቼ ረቂቁን እርሳቸው እንዲያዩት በጸሐፊቸው በኩል ላኩላቸው፡፡   ክቡርነታቸው ደብዳቤው እንደደረሳቸው ስልክ ደወሉልኝና ነገ 4 ሰዓት ቢሮአቸው መምጣት እችል እንድሆን ጠየቁኝ፡፡ እኔም መምጣት እንደምችል ነግሬያቸው ተለያየን፡፡ ቀጠሮ ላይ ቀልድ የማያውቁት ፕ/ት ግርማ በነገታው 4...

ከካፋ ደን እስከ ሃርቫርድ ደጅ፦ የጀበና ቡና ለአእምሮ እርጅና ፍቱን መድኃኒት?

በኢትዮጵያ ምድር የቡና መዓዛ የማይሸትበት መንደር፣ የጀበና ድምፅ የማይሰማበት ቤት፣ ወይም "ቡና ይቅረብ" የማይባልበት እንግዳ ማግኘት የማይታሰብ ነው። ቡና ለእኛ መጠጥ ብቻ አይደለም፤ የታሪካችን ድርና ማግ፣ የማህበራዊ ህይወታችን የጀርባ አጥንት፣ እና የዕለት ተዕለት የትውስታችን...

ዛሬ የዓለም አፈር ቀን ነው፤ አፈራችሁን ጠብቁ ከአፈር የተሰራን፣ ወደ አፈር የምንመለስ ነን

ዛሬ ዓለም የአፈር ቀን ያከብራል። ያለ አፈር ሀገር የለም። በቅንጡ ግንባታዎች መኖር የምንችለው አፈር ሲኖር ነው። የመስታወት ህንፃዎቻችን ያለ አፈር አያኖሩንም። አፈር ነን፤ በገዛ ወገናችን እንጨክናለን ስለ አፈር ግድ አይሰጠንም። ለዚህ ነው የአፈር ቀን...

“እዚህ የአበሻ ቀጠሮ የለም” ኢትዮጵያ ውስጥ ያደገችው ኖርዌያዊት ሀኔ

ምናልባት ማህበራዊ ሚዲያ የሚከታተሉ ወጣቶች ሀኔን በምትሰራቸው ቪዲዮዎች ያውቋት ይሆናል። የሮርዌይ ዜጋ ስትሆን አማርኛ ትናገራለች። ከእጇ ላይም የቡና ስኒ አይጠፋም።ብዙዎች ቲክቶክ እና ኢንስታግራም ላይ „desyemil.amharic  „ወይም „ሀኔ “ በሚል ስሟ ያውቋታል። ቲክቶክ ላይ በአጭር...

መጽሔቶች

ዜናዎች

spot_imgspot_img
በቅርብ የወጡ ጽሑፎች