የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች፣ የኪነ ጥበብ ሰዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች በአማራ ክልል እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ አቅራቢያ የተገነባውን የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የስራ እንቅስቃሴን እየጎበኙ ነው።
ለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከ1ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩ የተጠቆመ ሲሆን፤ ለለሚ ከተማ መስፋፋትም ዋነኛ የልማት ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።
ፋብሪካው ባለፉት ስድስት ወራት ከ12 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሲሚንቶ ምርትን ለገበያ ማቅረብ መቻሉም ታውቋል፡፡
በዚህም ገበያውን ከማረጋጋት ባሻገር በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ ተጨባጭ መነቃቃትን መፍጠሩ ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካን መስከረም 18 ቀን 2017 ዓም መርቀው ስራ ማስጀመራቸው ይታወሳል።
ፋብሪካው በኢትዮጵያዊው ኢስት አፍሪካ ሆልዲንግና በቻይናው ዌስት ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ በሽርክና የተገነባ ሲሆን በቀን አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ የማምረት አቅም ያለው ነው።
ኢዜአ
