ለኩላሊት ህሙማን ታካሚዎች መድሃኒት ማቅረብ አልቻልኩም ሲል የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል አስታወቀ

Date:

በዋናነት ለትግራይ ክልል፣ በሪፈር ደግሞ ከአማራ እና አፋር ክልሎች ለሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎት የሚሰጠው በመቀሌ የሚገኘው የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል፣ የመድኃኒት እና የላብራቶሪ መመርመሪያ ግብዓቶች እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ አሁንም ችግር ሆኖ እንደቀጠለበት ገልጿል፡፡

በክልሉ ተካሂዶ በነበረው ጦርነት በርካታ ችግሮች አጋጥመውት የነበረውና አሁንም ወደ ቀድሞው ቁመናው ያልተመለሰው ሆስፒታሉ በተለይም ለኩላሊት ህክምና የሚያገለግሉ መድሃኒቶች ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ቢጨምርም መድኃኒቶቹን ማግኘት የማይቻልበት ደረጃ ላይ እንደደረሰ የአይደር ሆስፒታል የፋርማሲ ክፍል ዳይሬክተር አቶ ጣዕመ ተናግረዋል።

በተለይ በክልሉ ለሚገኙ የኩላሊት ታማሚዎች የሚሆን ምንም አይነት የመድሃኒት እቅርቦት እንደሌለ ነው አቶ ጣዕመ ለጣቢያችን የገለፁት፡፡

ሆስፒታሉ ለህሙማኑ የላብራቶሪ አገልግሎት እየሰጠ ቢሆንም የተሟላ አለመሆኑን አንስተዋል፡፡

በክልሉ የሚገኙ በርካታ ሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች በጦርነቱ ወቅት በደረሰባቸው ውድመት እና ዝርፊያ ምክንያት ከወትሮው በተለየ በሆስፒታሉ ላይ ጫና በርትቷል ያሉት ዳይሬክተሩ፣ ከመድሃኒቶች በተጨማሪ የላብራቶሪ መመርመሪያ ግብዓቶች እጥረትም በከፍተኛ ሁኔታ ማጋጠሙን ተናግረዋል፡፡

በትግራይ የኩላሊት ሕሙማን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃፍቶም አባዲ በበኩላቸው፣ ህሙማኑ በገንዘብ እጥረት ምክንያት የከፋ ችግር ላይ ይገኛሉ ያሉ ሲሆን፣ የመድሀኒት አቅርቦት በቅርቡ ቢኖርም ዋጋው ግን የሚቀመስ አይደለም ብለዋል።

በትግራይ ብቸኛው የኩላሊት እጥበት (ዲያሊሲስ) ማድረጊያ ቦታ በአይደር ሆስፒታል እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ሃፍቶም ፣ አሁን ላይ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገልግል አንድ መድኃኒት እስከ 3ሺ 9 መቶ ብር ድረስ እየገዙ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

@ኢትዮኤፍኤም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከባለፈው  ዓመት የ130 በመቶ ብልጫ  አተረፈ

መጋቢት 30 በተጠናቀቀው የኩባንያው በጀት ዓመት 15.9 ቢሊዮን ብር...

በዕውቀቱ በታላቁ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ተመረጠ

ዝነኛው ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...