ለ1447ኛውን የዒድ አልፈጥር ረመዳን በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሚከናወነው የዒድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ፡፡
በዚህም መሰረት፡-
👉ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች (ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች በተመሣሣይ ከቦሌ በአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ለሚሄዱ አትላስ መብራት እና ፒኮክ መብራት ላይ፤
👉 ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ ለሚሔዱ አሽከርካሪዎች (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)፤
👉 ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ለውስጥ ወደ ጋዜቦ አደባባይ ለሚመጡ (ጋዜቦ አደባባይ ላይ)፤
👉 ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ ሳንጆሴፍ መብራት ለሚመጡ ለከባድ ተሽከርካሪዎች (አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ) ሲሆን ለሌሎች ተሽከርካሪዎች (ጥላሁን አደባባይ ላይ)፤
👉 ከቡልጋሪያ መብራት ወደ ገነት ሆቴል ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች (ቡልጋሪያ መብራት ላይ)፤
👉 ከልደታ ፀበል ውስጥ ለውስጥ ወደ አሹ ስጋ ቤት የሚያስወጣው (ልደታ ፀበል ላይ)፤
👉 ከጦር ኃይሎች በከፍተኛ ፍ/ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሔዱ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ላይ)፤
👉 ከአብነት አካባቢ በፈረሰኛ ፖሊስ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ መብራት (ፈረሰኛ ፖሊስ ካምፕ መብራት ላይ)፤
👉 ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር መውረጃ (ሞላ ማሩ መታጠፊያ ላይ)፤
