መረጃ በማይሰጡ ኃላፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያስችል ሕግ ተዘጋጀ

Date:

የመገናኛ ብዙሃን እና የመረጃ ነፃነት የየራሳቸው ባህሪ ቢኖራቸውም እስካሁን የመገናኛ ብዙሃን እና መረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 በሚል በአንድ ላይ ተጣምረው ቆይተዋል።

ይህ ደግሞ ግልጽ የአሰራር ስርዓት እንዳይዘረጋ ማድረጉን የተናገሩት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ፤ የመረጃ ነፃነት ረቂቅ አዋጅ ለብቻው ተረቅቆ መቅረቡን ገልጸዋል።

ሰባት ክፍሎች እና 60 አንቀጾችን የያዘው ይህ የመረጃ ነፃነት ረቂቅ አዋጅ ፤ በዋናነት አዋጁን የማስፈጸም ሙሉ ስልጣን ለኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ይሰጣል። ማንኛውም ዜጋ መረጃ በሚጠይቅበት ወቅት መረጃ በማይሰጡ ኃላፊዎች ላይ ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑም ተገልጿል።

ረቂቅ አዋጁ የመንግስት ተቋማትን ብቻ ሳይሆን ከህዝብ አገልግሎት ጋር በቀጥታ የሚገናኙ የግል ድርጅቶችንም ጭምር መረጃ እንዲሰጡ የሚያስገድድ አንቀጽ ማካተቱ በጥንካሬ ተነስቷል። ይህም ጥሩ ድንጋጌ መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ረቂቅ አዋጁ ይፋ የማይደረጉ መረጃዎች በማለት በአንቀጽ 18 ላይ በዝርዝር ያስቀመጠው ድንጋጌ የክርክር መነሻ ሆኗል። በዚህም መሰረት የመከላከያ እና የሀገር ደህንነት መረጃዎች ፣ የፍርድ ቤት ምርመራ ሂደቶች እና የድርጅት ሚስጥሮች የህግ ጥበቃ እንደሚያገኙና ይፋ እንደማይደረጉ ይገልጻል።


የምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ደሳለኝ ይህ አንቀጽ ለተለያየ ትርጉም የተጋለጠ በመሆኑ እና ለብልሹ አሰራር ምቹ ሁኔታ ሊፈጥር ስለሚችል በዝርዝር እንዲታይ ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል።

አሐዱ በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡበት ጠበቃ እና የህግ አማካሪ የሆኑት አቶ ዳንኤል ፍቃዱን አነጋግሯል። የህግ ባለሙያው የረቂቅ አዋጁ ዋነኛ አላማ ሁለቱን አዋጆች መለያየት መሆኑን አብራርተዋል።

በአዋጁ ከተካተቱ መሰረታዊ ድንጋጌዎች መካከል የመንግስት ኃላፊዎች ተጠያቂ የሚሆኑበት እና መረጃ የሚሰጡበት ጊዜ ገደብ መወሰኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም ጋዜጠኞች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳይታሰሩ የሚያግድ ድንጋጌ መካተቱንም ገልጸዋል።

አዋጁን የማስፈጸም ስልጣን ለህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም መሰጠቱን የገለጹት የህግ ባለሙያው ትችት በቀረበበት የደህንነት መረጃዎች አያያዝ ዙሪያም አስተያየታቸውን ሲሰጡ አዋጁ ወደ ፊት ሲጸድቅ የትኛው መረጃ በሚስጥርነት እንደሚፈረጅ ግልጽና በማያሻማ መንገድ ሊቀመጥ ይገባል ብለዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንን መረጃ የመጠየቅ ፣ የማግኘት እና የማስተላለፍ ጉዳዮችን የሚመለከተውን የመረጃ ነፃነት ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 10/2018 ሆኖ ለተጨማሪ ምርመራ መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ/ም ለዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መምራቱ ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የ30 ዓመታትን ጉዞ የሚዘክረው ዳሸን ኤክስፖ

የዳሸን ባንክን 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው...

‹‹ሀገር ጥለው የጠፉና ድርጅቶቻቸውን ለመዝጋት የተገደዱ አሉ››

አቶ አለማየሁ ከተማ(የኢትዮጵያ ሪልስቴት አልሚዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት) ግዮን መጽሔት :-...

የሰላም ስምምነት ሳይፈጸም የንግድ መርከቦች ጉዞ እንደማይጀምሩ የነዳጅ ጫኝ ኩባንያ ኃላፊ ተናገሩ

የሲውዲን ነዳጅ አጓጓዥ ኩባንያ የሆነው ‘ስቴና በልክ’ ዋና ስራ...

የታሪካዊው ቁልቢ ገብርኤል የዕድሳት ጥሪ ፦ የ134 ሚሊዮን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት

! ከተገነባ 64 ዓመታትን ያስቆጠረውና በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናን የሚሳለሙት...