አፍሪካ ሊደርሺፕ ማጋዚን በሚያዘጋጀው ዓመታዊ የ2025 የአፍሪካ አመራር ሽልማት ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በተለያዩ ዘርፎች በእጩነት ቀርቦ ነበር።
ከነዚህም መካከል የአፍሪካ ኢንደስትሪ ዘርፍ አመራር ሽልማትን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጀማል አህመድ አሸንፈዋል።
አቶ ጀማል የአፍሪካ የኢንደስትሪ መሪነትን ከታንዛኒያው የነዳጅ ኩባንያ አመራር ጋር በጥምር ነው ያሸነፉት።
አቶ ጀማል አህመድ ኢትዮጵያዊውን ግዙፍ ተቋም እየመሩ ሚድሮክን በአፍሪካ ከሚጠቀሱ ውጤታማ ኩባንያዎች መካከል አሰልፈውታል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከአግሮ ኢንደስትሪ አንስቶ፣ በምግብ ማቀነባበር፣ በብረታብረት፣ በኮንስትራክሽን ማቴርያልስ፣ በአልባሳት ምርት፣ በኬሚካልና ፋርማሱቲካል ማንፋክቸሪንግ የተሰማራ የኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ዘርፍ መሪ መሆኑ ይታወቃል።
በሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ መሪነት ሶስት አስርት አመታትን በኢትዮጵያ ልማት ያሳለፈው ሚድሮክ ከአፍሪካ ግዙፍና አርአያ ተቋማት መካከል በመሆን ታላላቅ ክብሮችን እየተቀዳጀ ይገኛል።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጀማል አህመድ የአፍሪካ ሊደርሺፕ ማጋዚን ሽልማታቸውን በቅርቡ በለንደን እንደሚቀበሉ ይጠበቃል።
