በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

Date:

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት ሳምንት መራዘሙን አስታወቁ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የእስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም በሦስት ሳምንት መራዘሙን አስታወቁ።

በሁለቱ አገራት መካከል በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ውይይት ላይ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጄዲ ቫንስ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዩ መገኘታቸው ታውቋል።

ውይይቱ “በጥሩ ሁኔታ” ተካሄዷል ያሉት ፕሬዚዳንቱ “ዩናይትድ ስቴትስ ሊባኖስ ራሷን ከሄዝቦላህ መከላከል እንድትችል በጋራ ትሠራለች” ብለዋል።

የዚህ “ታሪካዊ ውይይት” ተሳታፊ መሆን “ትልቅ ክብር” እንደሆነ የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ወደፊት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የሊባኖሱን ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውንን ለመቀበል በጉጉት እንደሚጠባበቁ ተናግረዋል።

ትራምፕ፣ የሊባኖሱ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በመጪዎቹ ሳምንታት ወደ ዋይት ሐውስ እንደሚመጡ ተናግረው አገራቸው ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ማደራደር እንደምትፈልግ ገልጸዋል።

“ስለ ሄዝቦላህ ማሰብ አለባቸው” ያሉት ትራምፕ፣ “በዚያች አገር ነገሮችን ለማስተካከል ከሊባኖስ ጋር እንሰራለን” ሲሉ ቃል ገብተዋል።

አክለውም “ኢራን ውስጥ ከምንሰራው ጋር በአንድ ላይ እንዲሆን ማድረግ አስደናቂ ነገር ይመስለኛል” ብለዋል።

በአሜሪካ የሊባኖስ አምባሳደር ናዳ ሃማዴህ ሞዋድ፣ በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ዬቺኤል ሊተር፣ በሊባኖስ የአሜሪካ አምባሳደር ሚሼል ኢሳ እና በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሃካቢ

የሁለቱም አገራት ከፍተኛ ተደራዳሪዎቸ የተኩስ አቁሙ በመራዘሙ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

በአሜሪካ የሊባኖስ አምባሳደር ናዳ ሃማዴህ ሞዋድ፣ በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ዬቺኤል ሊተር፣ በሊባኖስ የአሜሪካ አምባሳደር ሚሼል ኢሳ እና በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሃካቢ እያንዳንዳቸው ትራምፕን በድርድሩ ውስጥ ላበረከቱት ሚና አወድሰዋል።

“ክቡር ፕረዚዳንት፡ በእርስዎ መሪነት ኢራን በጣም ተዳክማለች፤ ሄዝቦላህን የማዳከም እና ሊባኖስን ከወረራ ነፃ የማውጣት ዕድሉ እውን ነው” ያሉት ሌይተር፣ እስራኤል እና ሊባኖስ“ሄዝቦላህ ከተባለ ክፉ ተጽእኖ” ለማፅዳት ዓላማቸው አስተሳስረዋል ብለዋል።

ሃክካቢ ሄዝቦላህን በሰፈር ውስጥ በሁሉም ሰው መስኮት ላይ ድንጋይ ከሚወረውር ልጅ ጋር በማመሳሰል ገልጸውታል።

ሕፃኑን ማስቆም ከተቻለ በኋላ፣ እንደ ሊባኖስና እስራኤል ያሉ ሌሎች ጎረቤቶች በሰላም ይኖራሉ ሲሉም ያላቸውን ተስፋ ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

ከ 50 ሚሊዮን በላይ መራጮች በማንዋልና በዲጂታል ተመዝግበዋል

ከየካቲት 28_መጋቢት 28 የመራጮች ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበር ይታወቃል። በተለያዩ ጉዳዮች...