የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል በሰውነቱ ላይ አላስፈላጊ የስብ ክምችትን ወይም በህክምና ስያሜው ‘Madelung’s Disease’ የነበረበትን የ40 ዓመት ግለሰብ የቀዶ ጥገና ህክምና በተሳካ ሁኔታ ማከናወኑን ገልጿል።
የቀዶ ጥገና ህክምናውን ዶ/ር ኦብሳ ቢራቱ ሲመሩት ለማጠናቀቅ 5 ሰዓታትን ፈጅቷል።
ግለሰቡ በአንገቱ አካባቢ የተከማቸው ስብ ወደ ደረቱ ወርዶ የመተንፈሻ ችግር እንዲገጥመው አድርጎት ነበር።
ከቀዶ ጥገናው በኋላ 3.5 ኪሎ ግራም ክብደት ያለው ስብም ከሰውነቱ ወጥቷል።
ታካሚው ከቀዶ ጥገናው በኋላ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል።
የቀዶ ጥገናውን ያከናወኑ ሃኪሞች ቡድን
- ዶ/ር ኦብሳ ቢራቱ
- ዶ/ር ሲንቦና አራርሳ
- ዶ/ር ብርሃኑ ንጉሴ
እንደዚሁም በአንኤስቴሺያ ዶ/ር ኡስማን እና ዶ/ር መኩሪያ ተሳትፈዋል።
በነርስነት አብዲ፣ ዲቤ፣ ዋቅጅራ እና ተሬሳ የተባሉ የጤና ባለሙያዎች ስለመሳተፋቸው የአምቦ ዩኒቨርስቲ ገልጿል።
