በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የአለም ክፍሎች በተካሄዱ የጎዳና ላይ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተቀዳጅተዋል ።
በቦስተን የ5 ኪሎሜትር ውድድር አትሌት ገላ ሀምበሴ 14 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ በመግባት በአንደኝነት አሸንፋለች ።
በውድድሩ ላይ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ፣አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ 4ኛ ፣አትሌት ለምለም ሀይሉ 5ኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቀዋል ።
በሻናይ ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ፈታ ዘርአይ በቀዳሚነት አሸንፋለች ።
አትሌት ፈታ 1ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በመግባት የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል
ማሸነፍ ችላለች።
በሀር ቺንዶ ማራቶን በሴቶቹ አትሌት ብዙአለም ጨቅሌ አሸንፋለች።
አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት ከ30ደቂቃ ከ33ሰከንድ ወስዶባታል።
ፀሐይ ገብሬ በስድስት ሰከንዶች ዘግይታ ሁለተኛ ወጥታለች።
በወንዶቹ አትሌት ሞላልኝ ፋንታሁን 2 ሰዓት ከ12 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ ውድድሩን በማጠናቀቅ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
