ተመድ በመላው አለም አሁን ላይ ከ1 ቢሊየን በላይ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች እየተዘዋወሩ መሆኑን አንስቶ በዲጂታል ማኑፋክቸሪንግ ውስብስብ በሆነ መንገድ እየተመረቱም ነው ብሏል።
ተመድ በምዕራብ አውሮፓና ላቲን አሜሪካ የ3ዲ የጦር መሳሪያዎች እየጨመሩ መሆኑና በህገወጥ መንገድ መዘዋወር መቀጠላቸውን ጠቅሷል።
ድርጅቱ በድንበር አካባቢዎች ያለው የላላ ቁጥጥር የጦር መሳሪያ ማዕቀቦች እንዳይሰሩ አድርጓል ያለ ሲሆን ለማሳያነትም የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ባለባቸው ሊቢያና የመን የጦር መሳሪያዎች በአሸባሪዎች እጅ በቀላሉ እንደሚገባ አንስቷል።
የጦር መሳሪያ ዝውውሩ ሽብርተኝነት፣ የወንጀል ተግባራት እንደዚሁም ቀጣናዊ አለመረጋጋቶች እንዲጨምሩ እያደረገ ሲሆን ሁሉም አካላት ዝውውሩን በመግታት ስጋቱን ሊቀንሱ ይገባል ተብሏል።
መረጃው የአፍሪካ ኒውስ ነው።
@TikvahethMagazine
