በአርቲስት ጥላሁን ጉግሳ የተመሠረተው የቤት ስራ ማህበር የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ

Date:

ሀምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም፣ (ሀገሬ ቴቪ)፤ ‎በአርቲስት ጥላሁን ጉግሳ እና ወጣት ሀብታሙ አሰፋ መስራችነት የተቋቋመው ህብረት አምባ የቤቶች ማህበር ለሚያስገነባው የመኖርያ ቤቶች የመሰረት ድንጋይ በዛሬው እለት አስቀምጧል።

‎ማህበሩ ዛሬ የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጠው በጫካ ሲቲ አቅራብያ በሚገኘው 6ሺ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ሲሆን በቀጣይነትም ባሉት ከ20ሺ ካሬ ሜትር በሆነ ቦታ ላይ የመኖርያ ቤቶች ግንባታ እንደሚያከናውን አስታውቋል።

ማህበሩ ለግንባታ የሚጠቀማቸው ቦታዎች ቀድሞውኑ የማህበሩ ይዞታዎች ‎እስካሁን ከ150 በላይ ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን በቀጣይም በሺዎች የሚቆጠሩ መኖርያ ቤቶችን ገንብቶ ለነዋሪዎች የማስተላለፍ እቅድ ያለው መሆኑ ተገልጿል።

በዛሬው እለት የመሠረት ድንጋይ የተጣለለት የጋራ መኖርያ ቤት ህንፃ በሶስት አመት ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ ለባለቤቶቹ እንደሚተላለፍ ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሳልቫ ኬር ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት...

አሜሪካ ኤርትራ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ልታነሳ ነው !

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ አሜሪካ ከኤርትራ ጋር ያላትን ግንኙነት...

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ኅብረት የሰው ሠራሽ አስተውህሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ ሆነው ተሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአኅጉር ደረጃ ዘርፉን እንዲመሩ...

“የኒውክሌር ባለሙያዎች ከሌሉ ስምምነቱ አደገኛ ነው”

የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ካጃ ካላስ፣ በኢራን...