በኢትዮጵያ በቴሌግራም የሚደረግ የክሪፕቶ ግብይት (P2P Trading) ሊቆም ነው

Date:

በቴሌግራም ላይ ክሪፕቶ ግብይት መድረክ የሆነው ዋሌቴ (Wallet)፣ ከግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶችን (P2P Trading) እንደሚያቆም አስታውቋል።

ይህ ውሳኔ የተወሰደው የሀገሪቱን የፋይናንስ ህግ መሰረት አድርጎ እንደሆነ ነው የገለጸው።

ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ሁሉም በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የP2P ማስታወቂያዎች በሙሉ ይጠፋሉ ፤ አዲስ ማስታወቂያዎችንም መለጠፍም አይቻልም ተብሏል።

ከቀነ ገደቡ በፊት የተጀመሩ ግብይቶች በተለመደው አሰራር መሠረት መፈጸም እንደሚቻል ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም ፦
– ቢትጌት
– ባይናንስ
– ኦኬኤክስ
– ባይቢት … የመሳሳሉ መድረኮች በኢትዮጵያን ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶች (P2P) ማቆማቸው ይታወሳል።

አሁን ደግሞ በP2P ግብይት በስፋት የሚታወቀው የቴሌግራም ዋሌት ከግንቦት 25 በኋላ ያቆማል።

ብሔራዊ ባንክ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሥርዓት ያለው የዲጂታል ፋይናንስ ተሳትፎ እንዲኖር የሚያስችል አጠቃላይ የቁጥጥር ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ከዓለም አቀፍ አቻ ተቆጣጣሪዎችና ከአገር ውስጥ ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ መሆኑን መግለጹም ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...