በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዲጂታል ሎተሪ ይፋ ሆነ

Date:

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እንደገለፀው ይህ ዘመናዊ ሎተሪ ከወረቀት ሎተሪ በተጨማሪ በዲጅታል መላ በሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጥ ነው ብሏል።

በዲጂታል ሎተሪ ለረጅም ዓመታት በመፋቅ እድለኛ የሚያደርጉት የፈጣን እና የቢንጎ ሎተሪዎችም በዲጅታል መንገድ እንደተካተቱ ተገልጿል።

ከሀምሳ ሚሊዮን ብር ሽልማት አንስቶ በርካታ የጨዋታ አማራጮችን የቀረበበት  ሲሆን በስምንት የሀገራችን ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አገልግሎት ይህንን የዲጂታል ሽግግር ለማሳካት ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽንስ ከተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር  እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

አገልግሎቱ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዲጅታል ሎተሪ በተጨማሪ በሃምሳ ሺህ ብር ሽልማት የከፈተውን የእድል በር ወደ ሃምሣ ሚሊየን ብር ከፍ ለማድረግ እንደበቃም ተናግሯል።

ቀዳሚ ጽሑፍ
ቀጣይ ጥሑፍ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...