በእስራኤል ታሪክ የመጀመሪያው ጥቁር ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሰር!

Date:

ፕሮፌሰር አንበሰ ተፈራ ትውልድና ዕድገታቸው በኢትዮጵያ ሲዳማ ክልል ቦርቻ ወረዳ ነው። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሥነልሳን (Linguistics) አግኝተዋል። በዩኒቨርስቲው በመምህርነት ሙያም አገልግለዋል።

ፕሮፌሰሩ እ.ኤ.አ በ1989 ወደ እሥራኤል ሀገር በማቅናት የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከኽብሪው ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል፡፡ በእስራኤል ሀገር  በኽብሪውና በተል አቭቪ ዩኒቨርስቲ ከ15 ዓመታት በላይ በመምህርነት አገልግለዋል።

በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው በዕብራይስጥ ባህልና ቋንቋ ጥናት፣ በአረብኛ፣ በአማርኛና በሲዳማ ቋንቋ ጥናት ፈር ቀዳጅ መምህርና ተመራማሪም ናቸው። ከዚህም ባሻገር በእስራኤል ትምህርት ሚኒስቴር የአማርኛ ቋንቋ ትምህርትና ጥናት አማካሪ በመሆንም ያገለገሉ ታላቅ የቋንቋ ልሂቅ ናቸው።

ፕሮፌሰር አንበሰ ተፈራ በአካዳሚክ ዓለም ቆይታቸው ከ20 በላይ የምርምር ጽሑፎችን አሳትመዋል። ሦስት መጽሐፍት ጽፈል። የሲዳምኛ ሙሉ ሥነልሳን ከዛሬ 25 ዓመት በፊት በማጥናት ለሲዳሙ አፎ እድገት ሳይንሳዊ መሠረት የጣሉ የሲዳማ ህዝብ የምንጊዜም ባለውለታ ናቸው።

እኚህ የቋንቋ (የሥነልሳን) ተመራማሪ፣ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ፣ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከተቀበሉ ከ15 ዓመታት በኋላ በማግኘት፣ በእስራኤል ሀገር ታሪክ የመጀመሪያው ጥቁር፣ የመጀመሪያው  ኢትዮጵያዊ ሆነዋል፡፡

ፕሮፌሰሩ ከበርካታ ዓመታት በኋላ ወደ  ትውልድ መንደራቸው ሲመጡ ታላቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...