በኦሮሚያ ዜግነት አገልግሎት ከ30ሺህ በላይ ቤቶች ሊገነቡ ነው

Date:

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ እንደገለጹት፤ በኦሮሚያ ክልል በ2018 በጀት አመት የክረምት የዜግነት አገልግሎት 30 ሺህ 444 የገጠር መምህራን መኖሪያ ቤቶች ይገነባሉ ብለዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት በትምህርት ዘርፍ  የዜግነት አገልግሎት 4420 ቡኡረ ቦሩ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ጠቅሰው 777 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም  መገንባታቸውን ገልጸዋል።

3 ሺህ 382 የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል ሥራ መሰራቱን ጠቅሰው በአጠቃላይ 45.6 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሥራ መሰራቱን አስረድተዋል።

ዘንድሮ 2 ሺህ 853 አዲስ ቡኡረ ቦሩ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት መታቀዱን እንዲሁም  1 ሺህ 577 ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን ለመገንባት መታቀዱን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ በበጀት አመቱ በክልሉ የትምህርት ዘርፍ  66.4 ቢሊየን ብር የሚገመት የክረምት የዜግነት አገልግሎት ሥራዎችን ለመስራት ታቅዷል ብለዋል። በክረምት የዜግነት አገልግሎት የክልሉ ህዝብ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጠይቀዋል ሲል የዘገበው ኢፕድ ነው፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...