በቤተክርስቲያናችን አምስት የመሥዋዕት ዓይነቶች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ መጥዎተ ርእስ ነው።
ይህም ራስን ለእግዚአብሔር መስጠት ማለት ነው። እመቤታችን ድንግል ማርያም ገና በ3 ዓመቷ እግዚአብሔርን በሚፈሩ ቤተሰቦቿ ዓማካይነት ራሷን ለእግዚአብሔር የሰጠችና በተሰጣት ጸጋ አምላክን በድንግልና ለመውለድ የቻለች ናት።
ታኅሣሥ 3 ቀን የእመቤታችንን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት በዓል በደመቀ ሁኔታ ስናከብር፤ አንደኛ የሦስት ዓመት ብላቴና በሕፃንነቷ የቤተሰቦቿን ፍቅር ሳትጠግብ፣ ከሞቀ ቤት ወጥታ ከካህናት ጋር መኖርን እንዴት እንደ ቻለች እናያለን።
ኢያቄምና ሐናም ለእግዚአብሔር የተሳሉትን ስዕለት ሳያመነቱ ለመፈጸም ያሳዩትን ቁርጠኝነት እናደንቃለን።
ከእመቤታችን፤ ራስን ለእግዚአብሔር መስጠት ከሐናና ኢያቄም ደግሞ ለእግዚአብሔር ለመስጠት የተሳልነውን በሙሉ ልብ ሆነን መስጠት እንዳለብን እንማራለን።
በዓሉን የሰላምና የበረከት በዓል ያድርግልን። የእመቤታችን አማላጅነቷ ከእኛ ጋር ይሁን። አሜን
ብፅዕ አቡነ ናትናኤል
የሚኒሶታ፣ የኮሎራዶ እና አከባቢዎች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
