ቮዳኮምና ስታርሊንክ በአፍሪካ ኢንተርኔትን ለማስፋፋት ተስማሙ

Date:

ሁለቱ ተቋማት በአፍሪካ የገጠራማ አካባቢዎች የኢንተርኔት ተደራሽነትን ለማስፋትና ለቢዝነሶች ፈጣን ኢንተርኔት ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ፈፅመዋል።

በስምምነቱ መሰረት የስታርሊንክ የሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎት በቮዳኮም የሞባይል ኔትዎርክ በኩል ሲሰጥ በገጠራማ አካባቢዎች ለሚገኙ ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማት ፈጣን አገልግሎት መስጠት ያስችላል።

በተጨማሪ ቮዳኮም የስታርሊንክን መሳሪያዎች እና አገልግሎቶች በአፍሪካ ለሚገኙት ቢዝነሶች የመሸጥ መብት ተሰጥቶታል።

ቮዳኮም በ2030 የደንበኞቹን ቁጥር 260 ሚሊየን ለማድረስ እየሰራ ሲሆን ስምምነቱ ይኸንን ራዕይ እንዲያሳካ ያግዘዋል።

ስታርሊንክ በ25 የአፍሪካ ሃገራት እየሰራ ሲሆን ስምምነቱ ሌሎች አዳዲስ ተጠቃሚዎችን እንደሚጨምርለት ታምኖበታል።

@TikvahethMagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...